House and Building Sale
የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አሰግደዉ ደስታ (5 ሰዎች) መካከል ባለው የአፈጻጸም ክስ በኮቱ ከተማ የሚገኝ 182 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤትን በሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
More tags
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሣሽ ፀደይ ባንክ እና በአፈ/ተከሳሽ እነ አሰግደዉ ደስታ /5ሰዎች/ መካከል ስለአለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈ/ተከሳሽ አሰግደዉ ደስታ ስም የተመዘገበና በኮቱ ከተማ የሚገኝ በምስራቅ ሽመልስ ዉጣባቸዉ፤ በምዕራብ አመዘነች ታደሰ፤ በሰሜን መንገድ፤ በደቡብ አበባየሁ ደምሴ የሚያዋስነዉ በ182 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 917,845.76 / ዘጠኝ መቶ አስራ ሰባት ሺህ ስምንት መቶ አረባ አምስት ብር ከሰባ ስድስት ሳንቲም/ ታህሳስ 04 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት በኮቱ ከተማ 01 ቀበሌ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል።
በመሆኑም፡-
1. ተጫራቾች ያሸነፉበትን 1/4 ገንዘብ በሲፒኦ ወዲያውኑ የማስያዝ ግዴታ አለባቸው።
2. ተጫራቾች ማንነታቸውን ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
3. ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው እንደፍርዱ ለማስፈፀም ነው።
4. ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል።
5. የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል።
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ደ/ብርሃን
Tender details
- Deadline: 2026-12-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-12-13 12:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: North Shewa Higher Court
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T07:36:11.000Z
- Source: Qelal Tenders