Equipment and Accessories
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢ ን/ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨረታው ተወዳድሮ ለማቅረብ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር መከፈላቸው የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አቅርቦት ጋር ተዛማጅነት ያለው ንግድ ፈቃድ በእቃ አቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ /TIN / መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም ሂሳብ ቁጥር 1000026941737 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ የግን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 መቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራች ለውድድሩ የሚያቀርቡት የጨረታ ዶክመንት ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማንኛውም ህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ የብር /30,000/ ሰላሳ ሺህ ብር/ CPO በወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ስም አሰርቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
5. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውሉን ማስከበሪያ አሸናፊ ከሆነባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ከኮሌጁ ከሚገዙት የጨረታ ዶክመንት ላይ በመሙላት ዋናው /ኦርጀናል እና ኮፒው ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ አድርገው በፖስታው ላይ የኮሌጁ ስም እና ጨረታ ቁጥር በመፃፍ የንግድ ድርጅቱ ስም እና ማህተም በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ
7. ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ ለውድድሩ ዋጋ ሞልቶ የሚያቀርበው ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት ላይ ብቻ ሲሆን በእያንዳንዱ የጨረታ ዶክመንት ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማደረግ አለበት።
8. ተጫራቾች ከጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO / ጨምሮ ማንኛውም መረጃዎች ለውድድር ከሚያቀርቡት ኦርጅናል የጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት።
9. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በተከታታይ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ይከፈታል፡፡ ጨረታ የሚከፈትበት እለት በአል ወይንም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
10. አሸናፊው ውል ተፈራርሞ ካጠናቀቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ኮሌጁ ድረስ አቅርቦ ማስረከብ ይኖርበታል።
11.ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
12.ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ሁኔታ ቫትን /የተጨማሪ እሴት ታክስ / ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ ተብሎ ይወሰዳል።
13.ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ፡- በስ.ቁጥር 011 365 8463 ይደውሉ
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በተከታታይ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-20 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በተከታታይ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Welkite Poly Technic College
- Bid bond: 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ) ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 06, 2026)
- Posted at: 2026-11-06T08:45:56.000Z
- Source: Qelal Tenders