House and Building Foreclosure
የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሪት ሄርሚላ ቴዎድሮስ እና የፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ ሜሮን ለገሰ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/109243 በ30/7/2016 ዓ/ም እና በኮ/ መ/ቁ/111438 22/08/2016ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ለማስፈፀም በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 274 በካ/ቁ/ወ13/027101/30/661/00 በሰናይት ወርቅነህ እና ሄርሚላ ቴዎድሮስ ስም በተመዘገበ ይዞታ ውስጥ ከሚገኙ ቤቶች ውስጥ ሁለት ከፍል ቤት ከነማድ ቤቱ፤ ሁለት ከፍል ዕቃ ቤቶች በብሎኬት የተሰሩ ሁለት ክፍል ቤቶች በብሎኬት የተሰሩ ሽንት ቤትና ሻውር ቆርቆሮ በቆርቆሮ የተሰራ አንድ ከፍል ቤት አጠቃላይ የቤቶቹ ስፋት 104.56 ካ/ሜ የሆነ አጠቃላይ የንፅፅር ድርሻ 121.83 ካ/ሜ በይዞታው ውስጥ የፍርድ ውሳኔ ያላረፈባቸው ቤቱ ያሉ መሆኑ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,083,125 (አምስት ሚሊዮን ሰማኒያ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሀያ አምስትብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል። ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.111438 በቀን ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 1,270,781.25 ( አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሰባ ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ አንድ ከ25/100) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስትየስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና · ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.P.O አሰርቶ በኢትዮያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-12-09
- Bid closing time: 14:30
- Bid opening: 2026-12-09 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T08:29:43.000Z
- Source: Qelal Tenders