Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለመምሪያውና በስሩ ለሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለመምሪያውና በስሩ ለሚገኙ ፖሊስ ጣቢያዎች እና ለስራ አገልግሎት የሚውል ልዩ ልዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑ ተጫራቾች ከስር በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን በሲፒኦ በመ/ቤቱ ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
- ሉት 1 የፅህፈት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
- ሎት 3 ኤሌክትሪክ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000.00
- ሎት 4 የቧንቧ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 4,000.00
- ሎት 5 ህንፃ መሣሪያ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 4,000.00
- ሎት 6 የህትመት ውጤቶች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 6,000.00
- ሎት 7 ቋሚ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
- ሎት 8 አልባሳት የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
- ሎት 09 የካምፕ መመገቢያ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000.00
- ሎት 10 የመኪና ኪራይ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000.00
- ሎት 11 የጉልበት ሰራተኛ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000.00
- ሎት 12 የመኪና እና የሞተር ጎማ የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 3,000.00
- ሎት 13 ህክምና መድሀኒት ሪኤጀንትና የህክምና እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 5,000.00
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በጨረታው ለመወዳደር ፍላጐት ያላቸዉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢነት ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ለተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ዘወትር በስራ ስዓት ከጠዋቱ 2፡30 አስከ 6፡30 ከቀኑ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ 5ተኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 11 የስራ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሠዓት ውጭ ዘግይቶ የደረሠ ተጫራች ተቀባይነት የለውም።
5. ጨረታዉ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 መምሪያዉ በሚያዘጋጀዉ ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በሚገኙበት ይከፈታል። ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጎልም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን እሽጉ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች እንደ አስፈላጊነቱ ናሙና/ሳምፕል የሚያስፈልጋችውን እቃዎች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸዉ ሎቶች ናሙና ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም አንዳንድ ዕቃዎች ዝርዝር የዕቃ መለያ ፕሮፖዛል ወይም (እስፔስፊኬሽን) እና ሥሪቱ ሀገር መጥቀስ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ውጭና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፋባቸዉን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፍፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። መስሪያ ቤቱ ተጫራቾች ከአሸነፉት እቃ ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. በአቅርቦትና በአገልግሎት አሠጣጥ ብቃትና ጥራት እንዲሁም በወቅቱ ማቅረባቸውን ከአሁን በፊት የተመሠከረለት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ቢሆን ይመረጣል።
10. በጉዞ ወቅት ወይም በርክክብ ወቅት የተበላሹና የተሰበሩ እንዲሁም የማይሰሩ እቃዎች ቢገኙ ወይም ተመሳስለው የተሰሩ እቃዎች ቢያስረክብ ተመላሽ የማድረግና በራሱ ወጪ የመተካት ግዴታ አለበት ለሠጠውም እቃዎች ዋስትና መስጠት ግዴታ አለበት።
11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት መድሃኒት የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ መሆን አለበት።
12. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ሲያስገቡ ግዥ ክፍል ባዘገጀው ፎርም ላይ ዋጋቸውን ማስገባት አላባቸው። በራሳቸው ፎርም ዋጋቸውን ካስገቡ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ።
13. መስሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
- አድራሻ ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጎማ ቁጠባ 5ኛ ፎቅ ግዥ አስተዳደር ክፍል ስልክ ቁጥር 0115-57-33-14 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 10:30
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 11 የስራ ቀናት በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
- Bid opening: 2026-11-20 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Police Commission
- Buyer's registered address: ኮልፌ ቀራዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ምሪያ ከጦርኃይሎች በስተግራ ቀለበት መንገድ ሲወርዱ የቀድሞው ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ሳይደርሱ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Nov 09, 2026)
- Posted at: 2026-11-09T12:14:07.000Z
- Source: Qelal Tenders