Disposal Sale
የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
1. በጨረታ የሚሳተፈው ድርጅት ከሆነ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል እንዲሁም ከዚህ ጨረታ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ገቢ የሚደረግ ገንዘብ በተጫራች ድርጅት ስም መሆን አለበት።
2. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 15 ላይ በተገለፀው ቦታ በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል ማህበር ስም በዳሽን ባንክ የሂሳብ ቁጥር 0122244971011 ወይም በንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000000933353 በማስገባት ያስገቡበትን የባንክ ስሊፕ በመያዝ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ፋይናንስ መምሪያ የገንዘብ ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ሠነዱን በተራ ቁጥር አራት ላይ በተገለፀው የሥራ ቀንና ሰዓት መሠረት መውሰድ ይችላሉ።
3. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
4 ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከቀኑ 8፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሸከርካሪዎችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ቃሊቲ አደባባይ/ መንገድ ትራንሰፖርት ማሰልጠኛ/ ወደ ሐና ማሪያም አቅጣጫ በቀኝ ጠርዝ 50 ሜትር በኩል የድሮ ዩናይትድ አዉቶ ጋራዥ ቢግ ኤም አፓረል እና ጋርመንት (BIG M) ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ተርሚናል ግቢ ውስጥ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ለሚሳተፉበት (ለሚገዙት) ለእያንዳንዳቸው ተሸከርካሪዎች ያስገቡትን ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርበታል።
6. ተጫራቾች ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ የተሸከርካሪ ዓይነትና የሠሌዳ ቁጥር ትይዩ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ከጨረታ ማስከበሪያ CPO ጋር በማካተትይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመረጡት ተሸከርካሪ ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ እና CPO በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በማስገባት መወዳደር ይችላሉ። የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ኦርጅናል CPO እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል።
7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መኪኖቹ በሚገኙበት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ቃሊቲ አደባባይ/ መንገድ ትራንሰፖርት ማሰልጠኛ/ ወደ ሐና ማሪያም አቅጣጫ በቀኝ ጠርዝ 50 ሜትር በኩል የድሮ ዩናይትድ አዉቶ ጋራዥ ቢግ ኤም አፓረል እና ጋርመንት (BIG M) ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ተርሚናል ግቢ ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሑድ ወይም የበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
8. በጨረታው አሸናፊ የሆኑት ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፍል ይኖርባቸዋል ሆኖም ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለየድርጅቶቹ ገቢ ይደረጋል።
9. የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዟቸው ተሸከርካሪዎች የስም ማዛወሪያ እና በመንገድ ትራንስፖርት ግምትና የሽያጭ ውል ልዩነት ካለ ለአገር ውስጥ ገቢዎች ሚኒስቴር የሚከፈል ወጪ በጨረታ አሸናፊዎች ይሸፈናል።
10. የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማኝኛውም ተጫራች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል።
11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ/ ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን ተሸከርካሪ ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግና የሽያጭ ውል በመዋዋል ተሽከርካሪውን ተረክቦ ማንሳት ይኖርበታል። ሆኖም ተሸከርካሪውን በተጠቀሰው ቀን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል።
12. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘውያ ጨረታ ማስከበሪያ CPO ለተጫራች ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት እንዲመለስ ይደረጋል።
13. በጨረታ ሰነድ ላይ በሚቀርበው ፖስታ ላይ የተሸከርካሪው ሠሌዳ ቁጥር እና መለያ ኮድ መፃፍ አለበት
14. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሱት ደንብና ሁኔታ አስገዳጅ ናቸው።
15. የጨረታ ሰነድ መሸጪያ ቦታ አዲስ አበባ ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግ.ማህበር ሰሚት ፋርማ ኪዩር ግቢ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ነው።
16. ድርጅቱ በማንኛውም ምክንያት ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 17-83-32-06 እና 09 11-19-00-03 ይጠቀሙ።
Tender details
- Deadline: 2026-11-25
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-25 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Midroc Investment Group
- Buyer's registered address: የካ አባዶ ኮንደሚንየም መግቢያ ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ኃ.የተ.የግ ማኅበር ቅጥር ግቢ
- Bid bond: 20% ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Fortune (Nov 08, 2026)
- Posted at: 2026-11-09T14:22:15.000Z
- Source: Qelal Tenders