Billboards and Digital Advertising

ዳሸን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የተለያዩ ቋሚ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሽያጭ DB/053/2019

ዳሸን ባንክ አ.ማ. በባንኩ የሚገኙ ያገለገሉ ቋሚ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታና ቦታ በሎት 1 ለሶስተኛ ዙር እና በሎት 2 ለአንደኛ ዙር በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

 ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች ቄራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህንጻ 3ኛ ፎቅ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል በመምጣት የጨረታውን መረጃ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ብቻ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
  2. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡ዐዐ እስከ 1ዐ፡ዐዐ ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡን ብረቶችን በባንኩ መጋዘኖችና ቦታዎች በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
  3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ ለሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 20 ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝና በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  4. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።
  5. ከላይ በተራቁጥር 4 የተገለፀውንየጨረታማስከበሪያዋስትናያላስያዘእናበ ሠነዱየተቀመጡሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
  6.  የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከ አዲስ አበባ ውጪ ከሆነ ከዳሸን ባንክ አ.ማ. ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣ ሆኖም በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ክፍያ በቶሎ ገቢ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ ክፍያው በዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች በተዘጋጀ ሲፒኦ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ በ1ዐኛው ቀን ማለትም ሕዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ በዐ6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ09፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባንኩ የንብረት ክምችትና ስርጭት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
  8. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ3 /ሶስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 2 /ሁለት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከባንኩ ጋር ውል መፈራረምና ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ከላይ በተገለጸው መሰረት ውል ካልፈረሙ ወይም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ግዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
  9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ንብረት በራሳቸው ወጪ በማጓጓዝ ውል በፈረሙ በ10 የሥራ ቀናት ዉስጥ በማንሳት ማጠናቀቃቸው ሲረጋገጥ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. ባንኩ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
  11. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-465 5552 ወይም 011-470 6065 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  12. ባንኩ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ዳሸን ባንክ አ.ማ.

አዲስ አበባ

ሎት 1 (ሶስተኛ ዙር ጨረታ)

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

SWICH

በቁጥር

26

2

METAL DETECTOR

በቁጥር

60

3

Kama Small Generator

በቁጥር

4

4

LOST AND FOUND DISPLAY BOARD

በጥቅል

በጥቅል

5

NOTICE BOARD

በጥቅል

በጥቅል

6

WALL CLOCK

በቁጥር

4

7

EPSON TERMAL PRINTER

በቁጥር

35

8

NOTE COUNTING MACHINE FOR TELLER

በቁጥር

17

9

MANAGERIAL TABLE

በጥቅል

በጥቅል

10

COMPUTER STAND TABLE

በጥቅል

በጥቅል

11

HIGH BACK SWIVEL CHAIR

በጥቅል

በጥቅል

12

STORAGE CABINET

በጥቅል

በጥቅል

13

LOW BACK SWIVEL CHAIR

በጥቅል

በጥቅል

ሎት 2 (አንደኛ ዙር ጨረታ)

ተ.ቁ

 የእቃው አይነት

መለኪያ

 ብዛት

1

Adding machine

በቁጥር

17

2

Cash box

በቁጥር

7

3

Computer stand table

በጥቅል

በጥቅል

4

Coffee table

በጥቅል

በጥቅል

5

Counter chair

በጥቅል

በጥቅል

6

Dixon shelf

በቁጥር

7

7

Fax machine

በቁጥር

2

8

File cabinet

በቁጥር

5

9

Guest chair

በጥቅል

በጥቅል

10

Guest chair 2 and 3 seater

በጥቅል

በጥቅል

11

High back chair

በጥቅል

በጥቅል

12

Lost and found display board

በቁጥር

2

13

Low back chair

በጥቅል

በጥቅል

14

Managerial table

በጥቅል

በጥቅል

15

Metal detector

በቁጥር

4

16

Multi-currency detector

በቁጥር

15

17

Note counting for teller

በቁጥር

117

18

Notice board

በቁጥር

2

19

Monitor

በቁጥር

13

20

System unit

በቁጥር

14

21

Kyocera printer

በቁጥር

6

22

Scanner

በቁጥር

50

23

Single pedestal table

በጥቅል

በጥቅል

24

Sofa

በቁጥር

10

25

Storage cabinet

በቁጥር

3

26

Wall clock

በቁጥር

2

27

Safe

በቁጥር

14

28

Fire resistant

በቁጥር

2

29

Kama big generator

በቁጥር

1

30

ATM

በቁጥር

14

 


Tender details

  • Deadline: 2026-11-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-11-20 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Dashen Bank S.C.
  • Bid bond: 20% ለእያንዳንዱ ዓይነት ምድብ
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Fortune (Nov 08, 2026)
  • Posted at: 2026-11-09T14:41:24.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders