Printing and Publishing
በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የበጀት መረጃ የሚገልፅ ቴምፕሌት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ ቁጥር 03/2017
በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የበጀት መረጃ የሚገልፅ ቴምፕሌት ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡
1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ አግባብነት ያለውና ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በፌዴስራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ ዌይብ ሳይት የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ከዌይብ ሳይት አትመው ከጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ የሚችሉ ወይም በክልሎች በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግዥው መጠነ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
5. ተጫራቾች ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ውስጥ በቢሮው የተዘጋጀውንና የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት ዘወትር በሥራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድና የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአግባቡ በማዘጋጀት በፖስታ አሽገው ጨረታው ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በሚቆይበት ቀን እስከ 11፡25 ሰዓት ድረስ በቢሮው ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ክፍት ሆኖ በሚቆይበት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ቀጥሎ ባለው 16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና/ንብ/አስ/ዳይሮክቶሬት ይከፈታል። 15ኛው እና 16ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በ3፡00 ሰዓት ተዘግቶ 3፡30 ሰዓት ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ ስም ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 በሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. የፋይናንሻል እና የተጠየቁት ህጋዊ ሰነድ እንደዚሁም ሲ.ፒ.ኦ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታው አየር ላይ መቆያ ጊዜ ከሚያበቃበት የመጨረሻው ቀን ጀምሮ ላሉት ለ60 ተከታታይ ቀናት የሚያገለግል መሆን ይኖርበታል።
9. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት በ05 ቀናት ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የአገልግሎቱን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ በመያዝ በ 15 ቀናት ውስጥ ውል መግባት የሚችሉ መሆን አለበት።
10. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር፡- 046-180-50-71 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-11-24
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የመጨረሻው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-25 09:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Southern Ethiopia Regional State Finance Bureau
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 /ሁለት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
- Posted at: 2026-11-10T08:46:29.000Z
- Source: Qelal Tenders