Other Sales

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት የተለይዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በሁለተኛ ዙር በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሁለተኛ ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኛ የወሰደውን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ክፍያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት ኪራይ ለመክፈል ባለመቻሉ በባንኩ ስም ተመዝግበው ደንበኛው ተከራይቶ የነበረውን እና ባንኩ ከተከራዩ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎች በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በተሻሻለው የካፒታል ዕቃ ኪራይ አዋጅ ቁጥር 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሁለተኛ ዙር በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተከራዩ ስም

የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ (በብር)

የንብረቱ ሁኔታ

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

የሐራጁ ደረጃ

1

ትዝታ፣ተሻለና ቤተሰቦቹ ዳቦና ኬክ አምራች ህብ/ሽር/ማህበር

1. Rotary Over 16 Tray የዳቦ ማኮፈሻ አንድ (01) Set

2. Volumetric Dough Divider የሊጥ ማከፋፈያ (01) set

3. Mixer የሊጥ መቀላቀያ (01) set

4.Proofer For Rotary oven with Steam Generator (01)Set

5.Molding Machine የሊጥ ቅርጽ ማውጫ (01) Set

6. Bread Slicer የዳቦ መቁረጫ አንድ (1) Set

7. French Bread Iray and Rottey for ATDF250 ሁለት (02) Set

8. Flat Iray with Trolley for ATDF 250 ሁለት (02)

9. Diesel Generator አንድ (01) Set ናቸው፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥ

9,373,294.86

አዲስ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ሸገር ከተማ ገላን ክ/ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ውስጥ

ታህሳስ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00

2ተኛ

የሐራጅ መመሪያ

1. የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ ወይም 20% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይቻላል፡፡ በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጨራቾች የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠ የውክልና ሰነድ እና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በማቅረብ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ የሐራጅ ጨረታው ይካሄዳል።

2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማህበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በሐራጅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል።

3. የሐራጁ አሸናፊ ንብረቶቹን ሙሉ ለሙሉ በካሽ/በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ላሸነፈ ተጫራች የንብረቱን የሽያጭ ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን እና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያዎችን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጅ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጅ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል።

4. ተጫራቾች በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆኑ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን የማሽነሪ ክራይ መስፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመክፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታው አሸናፊ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።

5. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ፤ ንብረቶችን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽያጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግስት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ በቅድሚያ በመክፈል ንብረቱን ይረከባል።

6. በሐራጅ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ተያያዥ የሆኑ ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

7. በሐራጅ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

8. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው እጅ በእጅ በሚደረግ ሽያጭ/cash/ ወይም በባንኩ የሊዝ ፖሊሲ አሰራር በመከተል በዱቤ ሽያጭ/Credit Sale/ የሚደረግ ሽያጭ ይሆናል።

9. ንብረቱን በባንኩ የካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት መሰረት የመከራየት ዕቅድ ያለው ተጫራች የባንኩን ካፒታል ዕቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ መስፈርት ስለማሟላቱ በቅድሚያ እርግጠኛ መሆንና በባንኩ ፖሊሲ እና መመሪያ መሰረት ባንኩ የሚያከናውነው የፕሮጀክት ጥናት ላይ የሚቀመጡ ቅድመ-ሁኔታዎችን መስማማት ይጠበቅበታል።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታህሳስ 01 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰአት እስከ 6 ሰአት ይካሄዳል።

11. የካፒታል ዕቃ ካለበት መጋዘን ወደሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣መትከያ፣ስራ ማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው/ተከራይ ይሸፍናል።

12. ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከጨረታው ቀን በፊት ባሉት ጊዜያት ቀጠሮ በመያዝ ከላይ በሰንጠረዡ በተጠቀሰው መሰረት ንብረቶቹን በሚገኙበት አድራሻ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል፡፡  ለተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-365-91-44 / 011-365-89-43 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሐራጁን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወልቂጤ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-12-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-12-10 12:00
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer's registered address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 20%
  • Published on: Addis Zemen (Nov 10, 2026)
  • Posted at: 2026-11-10T12:07:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders