Materials

በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ስር ያለው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር 02/2019ዓ.ም

በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ስር ያለው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን

  • ሎት 1 አላቂ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች .....የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 50,000.00
  • ሎት 2. የጽዳት እቃዎች........የጨረታ ማስከበሪያ በብር መጠን 10,000.00
  • ሎት 3 የቋሚ እቃዎች………..የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን 300,000.00
  • ሎት4 ለሕትመት መፅሐፍት ግዢ....የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን 5,000.00

ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድር ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፦

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. ተጫራቾች ጨረታውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

3. ተጫራቾች ጨረታቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የማይመስስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 3፡00 ሰአት በልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ይከፈታል።

6. የመከፈቻው ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ የስራ ቀን ታሽጎ ይከፈታል።

ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት በተወዳደሩባቸው ሎት 1 ሎት 2 ሎት 3 ሎት 4 ሎት ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መገለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7.ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች የሞሉት ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን መለየት አለባቸው።

8. የዘገየ ጨረታና ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸው እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ(ጥያቄ)

አድራሻ ልደታ ክ/ከተማ በወረዳ 09 ስር የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

ስልክ ቁጥር፡- 0115577520/0115578474

ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-21
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-23 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በ10ኛው (አስረኛው) ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 3፡00 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lideta Limat Elementary School
  • Buyer's registered address: ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ስር የሚገኘው ልደታ ልማት የመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
  • Posted at: 2026-11-11T08:34:50.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders