Stationery
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ ህትመት፣ የፅዳት እቃ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃ፣ መስተንግዶ እና HIV ሚኒስትሪሚንግ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesTextile, Garments and Uniforms
Amhara
More tags
Textile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureCatering and Cafeteria ServicesMedical Equipment and SuppliesHealth Care, Medical IndustryHealth Related Services and MaterialsAmharic2merkatoKalu Woreda Court
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ
- ሎት 2 የደንብ ልብስ
- ሎት 3 ህትመት
- ሎት 4. የፅዳት እቃ
- ሎት5. ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት6. ቋሚ የቢሮ እቃ
- ሎት7. መስተንግዶ እና HI V ሚኒስትሪሚንግ
ለ2019 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረትመወዳደር የምትችሉ መሆኑንእንገልጻለን።
በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች ሕጋዊ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ቲን ነበር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና መረጃ ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለባቸው።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው።
- ማንኛውም ተወዳዳሪ የሚሞሉት ዋጋ ከ500 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በማንኛውም ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒዎችን በመለየት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ከ02/03/2019 ዓ.ም ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11/03/2019 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት የተዘጋጀውን የማይመለስ ብር 100 / አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 4 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 11/03/2019 ዓ/ም በማስገባት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሠአት ላይ ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።ከተጠቀሰው ቀንና ሰአት ዘግይቶ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተነገራቸው በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም።
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰአት የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት የተቆረጠ ህጋዊ ደረሠኝ ማስያዝ የሚገባችሁ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ ከሆነ የቆይታ ጊዜው 60 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን መቻል ይኖርበታል።
- የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፣
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በፍትህ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።
- መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ከአሸነፈው ዕቃ ወይም ገንዘብ ላይ 30% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የአማራ ከልል ገ/ኢ/ት/ቢሮ ያወጣውን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 44/2018 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር ሆኖ ሳለ ፍ/ቤቱ የመንግስትን ጥቅም የሚያስከብር ሆኖ ካገኘው በተናጠልም የምናወዳድር መሆኑን መታወቅ አለበት።
- አሸናፊው ተወዳዳሪ የሚያቀርበው ዕቃ ጥራቱን የጠበቀ (ኦሪጅናል) ዕቃዎችን የማቅረብ ግዴታ አለበት
- ለተጨማሪ መረጃ በቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት በስ/ቁ 033-551-2961 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የቃሉ ወረዳ ፍ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-20
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-11-20 10:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kalu Woreda Court
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
- Posted at: 2026-11-11T09:18:38.000Z
- Source: Qelal Tenders