Disposal Sale
በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ያሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በሽያጭ አወዳድሮ ማስወገድ ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልፅ የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2019 ዓ.ም
በአብክመ ደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ያሉ ቁርጥራጭ ብረቶችን የመኪና ጎማዎችን የመኪና ቁርጥራጭ ብረቶችን እና የተቀደደ በርሜል ሌሎች እቃዎች እንዲሁም የተሰባበረ ወንበርና ጠረጴዛ በንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 145/2018 መስረት መ/ቤታችን በሽያጭ አወዳድሮ ማስወገድ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት አሟልታችሁ መጫረት ትችላላችሁ።
1. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው መ/ቤታችን በመገኘት ተጫራቾች ለሰነድ መግዥያ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ብቻ በመክፈል ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመንግስት የስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ በብር 15,000 መ/ቤታችን በወሰነው የጨረታ ዋስትና ማለትም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
3. በሁሉም ንብረት ክፍል ውስጥ ያለውን የመኪና ጎማ እና የመኪና ቁርጥራጭ ብረቶች እና የተቀደደ በርሚሎች በአካል በመሄድ እና በማየት የምትገዙበትን ዋጋ በመሙላት በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በማስገባት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝብ በዓላት ቀን ከሆነ ወደፊት ባለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033 116 01 99/54 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻችን፡- በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ወረኢሉ፤
የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-23 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Wereilu Woreda F/E/D/B
- Bid bond: 15,000.00 ብር በሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Nov 12, 2026)
- Posted at: 2026-11-12T08:43:19.000Z
- Source: Qelal Tenders