Building Construction
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለሠልጣኞች ለመማሪያ አገልግሎት የሚውል G+2 ታሳቢ G+0 መንታ ህንፃ እየተሰራ ሳይጠናቀቅ ቆሞ የነበረው በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ/የጨረታ መለያ ቁጥር ታፖቴኮ/05/2019 ዓ.ም
በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለሠልጣኞች ለመማሪያ አገልግሎት የሚውል G+2 ታሳቢ G+0 መንታ ህንፃ እየተሰራ ሳይጠናቀቅ ቆሞ የነበረው በጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ሊወዳደሩ ይችላሉ።
1. ህንጻ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 6 እና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
2. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ አለበት፣
4. የዘመኑ ግብር ስለመክፈሉ እና በጨረታ ይሳተፉ ደብዳቤን ከሚመለከተው አካል ማቅረብ አለበት፣
5. የጨረታ ሰነድ 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በኮሌጃችን የንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000042580647 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ቀርበው ከኮሌጃችን ግ/ን/አስ/ዳ/ት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ላይ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፣
6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ግልጽ በሆነ ስርዝ ድልዝ የሌለ በሚነበብ ጽሁፍ የድርጅቱን ስምና ፊርማ ማህተም፣ የስልክ ቁጥራቸውንና ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለበት፣
7. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ብቻ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ (CPO) በኮሌጃችን ስም በማዘጋጀት ከቴክኒካል መረጃ ፖስታ ጋር አንድ ላይ አያይዞ ማቅረብ አለበት፣
8. ተጫራቾች የቴክኒካል መረጃ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ፣ የፋይናንሻል መረጃ አሪጅናልና ሁለት የኦሪጅናል ኮፒ ለየብቻ አሽጎ በኮሌጃችን ግ/ን/አስ/ዳ/ት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02-16 ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በሥራ ሰዓት ቀርበው መክተት አለበት፣
9. የጨረታ ሣጥኑ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ከተቆጠረ በኋላ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት ሥራ ቀን ሆኖ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ አከፋፈት ሃደቱን አያስተጓጉልም፤
10. አሸናፊ የሆነ የሆነ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 7 የሥራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ዋስትና በማስያዝ ከኮሌጁ ጋር ውል መግባት አለበት፣
11. የጨረታ ማስታወቂያ የተጫራቾች መመሪያ ሆኖ ያገለግላል፣
12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በዳውሮ ዞን የታርጫ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-12-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-12-03 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: South West Ethiopia Region
- Publishing entity: Tarcha Polytechnic College
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 11, 2026)
- Posted at: 2026-11-12T08:55:31.000Z
- Source: Qelal Tenders