Building Construction

በአብክመ በደ/ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለሚያስገነባቸው የካፒታል ፕሮጀክት ግንባታዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም

በአብክመ በደ/ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለምናስገነባቸው የካፒታል ፕሮጀክት ግንባታ ሎት፡1 የወረኢሉ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ሲቪል ሰርቪስ ፑል ግቢ ውስጥ ስቶር ግንባታ፣ ሎት2፡የወረኢሉ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጭሳ ጤና ጣቢያ የኢመርጀንሲ ቢሮ ግንባታ፣ ሎት3፡የወረኢሉ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት 013 ቀበሌ ሞደል ጤና ኬላ ግንባታ፣ ሎት4፡የወረኢሉ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት 09 ቀበሌ ጤና ኬላ ካርድ ክፍል ግንባታ እና ሎት5 የወረኢሉ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ካቤ ከተማ መናሃሪያ አጥር፣ ቢሮና ዘበኛ ቤት ግንባታ በመደበኛ በጀት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ለዚህም የስራ ተቋራጮች ማሟላት ያለባቸው፡-

1. የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለበት የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል

3. የግዥ መጠን ከ500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይ ሰርትፊኬት ማቅረብ የሚችል

4. በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል

5. በግንባታ ሙያዎች ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 7 በG.C እና B.C በላይ የታደሰ የሙያ ስራ ፈቃድ ያላችሁ

6. የፋብሪካ እና የአካባቢ ማቴሪያል ችሎ ሙሉ ስራውን መስራት የሚችል

7. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በሰሯቸው ስራዎች የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ ይኖርባቸዋል

8. የግንባታውን ስራ ዝርዝር /bill of quantity/ እንዲሁም የግንታውን ዲዛይን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ

9. በተቋራጩ (በጨረታ አሸናፊው) ችግር ስራው ቢጓተት /ቢበላሽ/ ወይም ከተሰጠው ዲዛይን ውጭ መስራቱ በባለሙያ ከተረጋገጠ ለባከነው የአከባቢም ሆነ የፋብሪካ ማቴሪያል ኪሳራው በራሱ ሆኖ ጽ/ቤቱ ስራውን አስቁሞ ውለታውን አቋርጦ የተሻለ አማራጭ ይጠቀማል።

10. ተጫራቹ የጨረታ ማስከበሪያ ሎት፡1 በብር 50,000ብር፣ ሎት2፡ በብር 70,000ብር ፣ሎት3፡በብር 75,000 ሎት4 ፡ በብር 35000 ሎት5 በብር 20,000 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና እንዲሁም ሌተር ኦፍ ክርዲት ማስያዝ አለባቸው። የሚያሲዙት የዋስትና አይነት ቢያንስ ለ90/ ለዘጠና ቀናት/መቆየት አለበት፤፤ እንዲሁም የመጫረቻ ሰነድ ጸንቶ የመቆያ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት እለት ጀምሮ በሚቆጠር ለ 45 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፤፤

11. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተነካ ካለ ከጨረታ ውድቅ ይሆናል፤

12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ለእያንዳንዱ ግንባታ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመግዛት መሙላት ይችላሉ።

13. በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለ በጨረታው አሸናፊ ከሆነ ከተጫራቾች መካከል ከፍተኛ የሞላው ዋጋ በክፍት ቦታው ተሞልቶ ክፍት ለሆነው ስራውን በነጻ የሚሰራ ይሆናል።

14. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-5 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን መረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው የድርጅቱን ማህተም በሁሉም ኮፒዎች ላይ በመጠቀም እና የጨረታ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ዋና እና ኮፒውን በማያያዝ በጥንቃቄ በ2 ፖስታ ለየብቻ በማሸግ በወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በማስገባት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ21ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በይፋ ይከፈታል።

15. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፈቃድ የጨረታው ሂደት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል።

16. የጨረታ ማሸጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በህዝብ በዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ስዓት የሚታሸግና የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን።

17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 033 116 0199/54 መደወል ይችላሉ

18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

በአብክመ የደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-12-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ21ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-02 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በ21ኛው ቀን ከጧቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Wereilu Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ግንባታ
  • Published on: Addis Zemen (Nov 12, 2026)
  • Posted at: 2026-11-12T08:56:20.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders