Water Construction

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የጥልቅ ውሀ ጉድጓድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለደሴ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የጥልቅ ውሀ ጉድጓድ ለ015 ቀበሌ ልዩ ቦታው ኢድአድ ሲሆን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል።

 በዚህም መሰረት

  1. በጥልቅ ውሀ ግንባታ ስራ ፍቃድ ያለው
  2. ተጫራቾች ከደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸው።
  3. በግንባታ ከ2019 ዓ.ም የወጣ ንግድ ፈቃድ ከሆነ የመልካም ስራ አፈጻጸም መረጃ ማቅረብ አይጠበቅባቸውም። ነገር ግን ከ2019 ዓ.ም በፊት የወጣ ንግድ ፍቃድ ከሆነ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ሆኖም ግን ያልሰሩበትን ዓመተ ምህረት ካለ ከገቢዎች ዜሮ ሪፖርት ማቅረብ አለባቸው።
  4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
  5. የዘመኑን ግብር የከፈለ።
  6. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  7. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል።
  8. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ በመለየት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከወሰዱ በኋላ ዋጋውን ሞልተው ሲያስገቡ የቴክኒክና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. የጨረታው ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል። 
  11. ጨረታው ከ04/03/2019ዓ.ም እስከ 24/03/2019 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ይውላል።
  12. ጨረታዉ በ25/03/2019 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  13. ተጫራቾች ለሚሰሩበት ግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተመሰረተ ሲፒኦ፣ ቢድቦንድ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። እንዲሁም የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው። የውል ማስከበሪያ ካልያስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከለበሪያ 2% ፐርሰንቱ ይወረሳል።
  14. ተሸናፊ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ያስያዙት 2% ሲፒኦ ከአምስት ቀን በኋላ ይመለስላቸዋል።
  15. አሸፊው አካል ያሽነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያሲዝ ይሆናል።
  16. የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ።የተሰረዘ ካለ ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ። 
  17. የፌዴራል የብቃት ምስክር ወረቀት ያላቸው ከሆነ በክልሉ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የአጭር ጊዜ የብቃት ት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚጥል።
  18. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  19. የተጫራቾች መመሪያ በተመለከተ መመሪያው ብዙ ስለሆነ በሶፍት ኮፒ ከደ/ዙ/ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ መውሰድ አለባችሁ።

የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ / ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-12-04
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid opening: 2026-12-04 10:00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Dessie Surrounding Woreda F/E/D/B
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Nov 13, 2026)
  • Posted at: 2026-11-13T07:24:52.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders