Catering and Cafeteria Services

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም በግልጽ ጨረታ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ለሰራተኞች ምግብ፣ ትኩስና ለስላሳ መጠጦች አገልግሎት የሚያቀርብ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 002/2019

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የ2019 ዓ/ም በግልጽ ጨረታ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ለሰራተኞች ምግብ፣ ትኩስና ለስላሳ መጠጦች አገልግሎት የሚያቀርብ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

  • ሎት 1. የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ካፍቴሪያ አገልግሎት

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1- ለተጠቀሰው አገልግሎት በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።

2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3. ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።

4. ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራቾች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ሙሉ መደበኛ ጨረታ ሰነዱ መመለስ አለበት። ሰነዱን ያልመለሰ ከውድድር ውጪ ይሆናል።

6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከፓስተር አደባበይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመገኘት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከ0.5 እስከ 2 % 2,000 (ሁለት ሺህ)ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ መሙያ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሰነዱን ማቅረብ አለባቸው።

8.ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋ ከነቫቱ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ከፓስተር አደባበይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

9. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሸጎ በእለቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ተኛ ፎቅ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ውስጥ ይሆናል።

10. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። መድሀኒት ላይ ተቋሙ ያስቀመጠውን ዩኒት መሰረዝ፤ መቀየር አይቻልም።

ማሳሰቢያ-1. የምግብና የመጠጥ አገልግሎቱን ለሰራተኛው በኩቦን እየተቀበለ ቅድሚያ አገልግሎቱን ሰጥቶ የወሩ መጨረሻ ህጋዊ ደረሰኝ በማምጣት ክፍያውን ከጤና ጣቢያው ይወስዳል።

1, የተለያዩ ስብሰባዎች እና ስልጠናዎች ሲኖሩ ውሀ፤ ለስላሳ፤ ቆሎ እና ድፎ ዳቦ እንዲሁም ሻይ ቡና ትዛዝ ሲሰጥ ማቅረብ አለበት።

2, አሸናፊው ድርጅት ስራ ሲጀምር ጤና ጣቢያው ያስረከበውን ዕቃ በሀላፊነት መያዝ አለበት።

3. ተወዳዳሪ ድርጅት ጤና ጣቢያው ያቀረባቸውን የምግብና የመጠጥ አይነቶች ዋጋ መሙላት አለበት። ሁሉንም ካልሞላ ከውድድር ውጪ ነው የሚሆነው።

ስልክ ቁጥር፡- 011 895-9478 / 09 30-69-56-68 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-26 09:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Felege Meles Health Post
  • Buyer's registered address: አ/ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ወረዳ 06
  • Bid bond: ከ 0.5 እስከ 2% 2,000 (ሁለት ሺህ) ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 14, 2026)
  • Posted at: 2026-11-14T08:38:09.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders