Building and Finishing Materials

ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ የአካባቢ መልሶ ማገገም እና ኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ፕሮግራም የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ የአካባቢ መልሶ ማገገም እና ኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ፕሮግራም በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን በአንዳቤት ወረዳ እና በሰሜን ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ለፕሮግራሙ አገልግሎት የሚውል የልማት መሳሪያ የጋቢዮን ሳጥን፣ የችግኝ ማፍያ ፕላስቲክ፣ አዷማ፣ አካፋ፣ መዶሻ፣ መናኪሎ፣ የግንባታ እቃዎች፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ዘር፣ የጽህፈትና የጽዳት እቃዎች እንዲሁም የደንብ ልብስና ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በባሕር ዳር ዋና መ/ቤት ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. የሚገዙ እቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡ አቅራቢዎች እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ናሙና (ሳምፕል) ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
  5. አቅራቢዎች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በመምታት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በፖስታ ውስጥ አስገብተው በማሸግ የድርጅታችን ስም በመግለጽ በኢቨሎፕ ላይ በመፃፍ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የእቃዎቹን ዋጋ ሞልተው አስፈላጊ ሰነዶች ጋር በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የጨረታ ሰነድ መቀየር፣ ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
  8. የተሰረዘ፣ የተደለዘ፣ የተፋፋቀ ወይም በግልጽ የማይነበብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  9. የጨረታ አሸናፊዎች እቃዎቹን እስከ ዋና መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አድራሻ፡-ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ ዋና መ/ቤት ባሕር ዳር ቀበሌ 13 ትምህርት ቢሮ ጀርባ
  • ስልክ ቁጥር፡- 058 220 5160 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ የአካባቢ መልሶ ማገገም እና ኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ፕሮግራም


Tender details

  • Deadline: 2026-12-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-12-03 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ፍሎሬስታ ኢትዮጵያ
  • Bid bond: 1%
  • Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
  • Posted at: 2026-11-16T13:52:11.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders