Stationery
በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ፈርኒቸር እና የግንባታ ማቴሪያል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesCleaning and Janitorial Equipment and Service
Amhara
More tags
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksAmharic2merkatoAmhara Regional State Gonder Zone Farta Woreda Finance Office
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳዳር ዞን የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴክተሮች
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 3 የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣
- ሎት 4 የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣
- ሎት 5 ፈርኒቸር እና
- ሎት 6 የግንባታ ማቴሪያል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ክሊራንስ እና በወቅቱ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ስለጨረታው አጠቃላይ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለጽህፈት መሳሪያዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለጽዳት እቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ለቢሮ መገልገያ እቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ፣ ለኤሌክትሮኒከስ እቃዎች ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለፈርኒቼር ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለግንባታ ማቴሪያል ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በፋርጣ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ፖስታው ጋር አብሮ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው የሚገመገመው በመደበኛው የክልል የግዥ መመሪያ 144/2018 እና አዋጅ ቁጥር 306/2018 መሰረት ይሆናል፡፡
- በጨረታው አሸናፊው የሚለየው በጨረታ ሰነዱ የቀረበውን መነሻ በማድረግ ተገምግመው ከሚያልፉት ተጫራቾች መካከል በዋጋ ተነፃፅሮ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በአንድ ኢንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በቀረበው የዋጋ መሙያ ቅፅ ሞልቶ ማቅረብ የሚኖርበት ሲሆን የአንዱን የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ፣ ስምና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ከተለየ በኋላ ለእያንዳንዱ አቅርቦት የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና 10 በመቶ እና መ/ቤቱ ለሚከፍለው 30 በመቶ ቅድመ-ክፍያ ዋስትና በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ጋራንቲ (ሲፒኦ) ከህጋዊ ባንክ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን ከቀኑ 3፡30 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከጨረታ ሳጥን ከሚዘጋበት ከ3፡30 በኋላ የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የማይኖረው ሲሆን ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 3፡45 ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ማንኛውም ተጫራች ባቀረበው የማወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻል ማድረግ እና ራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል ፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆኑ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ መገምገሚያ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተ ጊዜ አንስቶ ለ45 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ግምገማው ከተቀመጠው ጊዜ በላይ የሚፈጅ ከሆነ ተቋሙ ዕጩ ተጫረቾችን የጨረታ ሰነድ ፀንቶ የሚቆይበትን ተጨማሪ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል፡፡
- በሁሉም ሎት አሸናፊው እንደተለየ እና የቅሬታ ማስተናገጃ ጊዜው በተጠናቀቀ 10 /አስር/ ቀን ውስጥ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል የሚያዝ ይሆናል፡፡
- እቃዎቹ የሚቀርቡት ፋርጣ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ባሉ ንብረት ክፍሎች ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሠነድ የመሸጫ ዋጋ 500 (አምስት ብር) ብቻ ነው፡፡
- የእቃዎች ርክክብ የሚፈፀመዉ በተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች ያወጡትን ወጭ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት የማይወስድ ይሆናል፡፡
- በማስታወቂያው ያልተገለጹ ነገሮች ካሉ በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 30 36 ደዉለዉ ወይም በአካል ፋ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-11-26
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡30
- Bid opening: 2026-11-26 09:45
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡45
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Regional State Gonder Zone Farta Woreda Finance Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500 ብር
- Published on: Be'kur (Nov 16, 2026)
- Posted at: 2026-11-16T14:16:37.000Z
- Source: Qelal Tenders