Freight Transport

ወማ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር በወልቂጤ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች በበልግና በመኽር ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል

Description

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ  ጨረታ ቁጥር 001/2019

ወማ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን /ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በቀቤና ልዩ ወረዳ በሚገኘው ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ አርሶ አደሮች በያዝነው በ2019/20 ምርት ዘመን በወልቂጤ ከተማ ከሚገኘው ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች በበልግና በመኽር ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።

ስለሆነ ተጫራቾች ከወማ የገ/ህ/ስ/ዩኒየን (ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር) በእያንዳዱ ቀበሌ የሚገኙ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፓልት መንገድ በአማካኝ በኩል በ1 (አንድ) ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

የጨረታ ዝርዝር መስፈርት
ክፍል አንድ አጠቃላይ የህግ እና የአሰራር መስፈርቶች

1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፤ የዘመኑ ግብር ከፍሎ ያሳደሰ እና እንዲሁም የግል ትራንስፖረት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው።

2. ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

3. የስራ ልምድ፡- ተጫራቹ በተለይ የግበርና ግብአቶችን (ማዳበሪያን) (ተመሳሳይ የጅምላ ጭነቶችን በማጓጓዝ ረገድ ቢያንስ የሁለት አመት ልምድ ያለው መሆን አለበት ከቀድሞ ደንበኞችን መልካም የስራ አፈጻጸም ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት።

4. ተጫራቹ ስራውን ለሌላ አካል በንዑስ ውል (subcontracting) ማስተላለፍ አይፈቀደለትም፡፡ በራሱ የሰራተኛን የተሽርካሪ አቅም ማሟላት አለበት።

5. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲመች በአንድ ልዩ ወረዳ በክፍል ዋጋ ማቅረብ እና መወዳደር አይችልም።

6. አጎራባች ወረዳዎችን ያሸነፈ የትራንስፖርት ድርጅቶች የተለያዩ በመሆናቸው ምክንያት በአጎራባች ወረዳዎች ስር በሚገኙ ማራገፊያ ጣቢያዎች መካከል የትራንስፖርት ዋጋ ልዩነት ከተፈጠረ ኪሎ ሜትርን መሰረት በማድረግ በአንድ ኪሎ ሜትር በተሰጠ ዝቅተኛ አማካኝ የአሸናፊ ዋጋ ይስተካከላል።

7. ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 10 ሥራ ቀናት መሁኑንና ጨረታው የሚከፈተው በቀን 17/3/2019 ዓ.ም መሆኑን እንገልጻለን።

ወማ ሁለገብ ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-11-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 10 ሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-11-26 12:00
  • Bid opening (note): 17/3/2019 ዓ.ም
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: የወማ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን
  • Published on: Addis Zemen (Nov 17, 2026)
  • Posted at: 2026-11-17T10:49:31.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders