Vehicle and Machinery Sale

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎቹን ከ11/03/2019 ዓ.ም ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል::

ማሳሰቢያ፦ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆንመተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፣

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች :-

  1. ለተሽከርካሪ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤ ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሸን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  2. በሐራጅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) በተለያዩ ባንክ በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩበትንም ሲ.ፒ.ኦ በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ለሐራጅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ያለው ከሆነ ከመነሻ ዋጋ ተነስቶ እንዲሁም መነሻ ዋጋ የሌለው ከሆነ ተጫራቹ የራሱን መነሻ በማስቀመጥ በኦንላይን በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  4. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሎ በዐ5 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፡፡
  5. ተሽከርካሪውን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ሶ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  7. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛሊሰጣቸው ይችላል፡፡
  9.  ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  10. የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 05 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ15/03/2019 ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11.  የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

NB:-

  • አሸናፊው ተጨማሪ ስሌት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ተሽከርካሪዎቹን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱም ሆነ ኦክሽን ኢትዮጵያ አማሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  • የሻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ሰሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-24 10:00
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Ethiopian Customs Commission
  • Buyer's registered address: በአባይ ማዶ ዲያስፖራ መንገድ ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአማራ ህንጻ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቢሮ ጎን
  • Bid bond: 200,000 ብር ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 20, 2026)
  • Posted at: 2026-11-20T06:58:26.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders