Tri Wheeler, Motorcycles and Bicycles Purchase

ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋሙ አ.ማ. ሞተር ብስክሌት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሚ የጨረታ ማስታወቂያ

ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋሙ አ.ማ. ሞተር ብስክሌት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን መስፈርቶች የሚታሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መሳታፍ ትችላላችሁ።

1. በዘርፍ የተሰማሩበትን የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ቫት የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።

2. ከፋይናንስና ኢ/ል/ቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋገጥ የምዝገባ ሰርቴፊኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Security) ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታው ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብቻ በመክፈል ከተቋሙ ፋይናንስ መምሪያ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጋዜጣው ከወጣበት አሥር/10/ ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የሚታሸግ ስለሆነ ተጫራቾች ወላይታ ሶዶ ወልማ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 1 መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

6. የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው ከወጣበት አሥር/10/ ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡45 ሰዓት በቢሮ ይከፈታል።

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 16 26 91 16

ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-11-30
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid closing (note): ጋዜጣው ከወጣበት አሥር/10/ ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-11-30 10:45
  • Bid opening (note): ጋዜጣው ከወጣበት አሥር/10/ ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Marchua Small Finance Institution S.C.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 20, 2026)
  • Posted at: 2026-11-20T07:50:32.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders