የቦታ ስፋት 455 ካ/ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመበት ዘነበወርቅ አሸኔ እና የፍ/ባለዕዳ አበራ ተድላ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/185975 በ6/2/2016 ዓ/ም እና በፌ/ከ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/315980 በ29/09/2016 ዓ/ም በኮ/መ/ቁ.198463 12/02/2017 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ/198463 በ30/4/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 463 የሆነ መለያ ኮድ AA 00005070218 በእነ አበራ ተድላ ስም ካርታ የተመዘገበ ያለው ሲሆን የቦታ ስፋት 455 ካ/ሜ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 23,230,790 (ሃያ ሦስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሠላሳ ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ፍ/ቤቶች


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Bid closing time: 11:00
  • Bid opening: 2026-05-08 11:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T09:38:25.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders