ዘመን ባንክ አ.ማ. ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ቤት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ የሐራጅ ማስታወቂያ

ዘመን ባንክ አ.ማ ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ቤት ባለበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990(እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪው

 ስም

የአስያዡ ስም

የንብረቱ አድራሻ

የቦታው ስፋት በሜትር ካሬ

የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር

የንብረቱ ዓይነት

የሐራጅ መነሻ ዋጋ

ሐራጅ የሚከናወንበት

ከተማ

/ከተማ እና ወረዳ

የቤት.

ቀን

የምዝገባ ሰዓት

የጨረታው ሰዓት

1

 ሽሬሻንሃይ ኢንዱስትሪ እና ትሬዲንግ /የተ/የግ/ማህበር

አቶ አወል አብዱራሂም ኢብራሂም እና / ባድራት አብደላ ኢብራሂም

አዲስ አበባ

ቦሌ /ከተማ፣ ወረዳ 08

 አዲስ

175  .

AA000060806472

ለመኖሪያ ቤት አገልግሎት የሚውል (G+1) ቤት

ብር 14,433,563.52 (አስራ አራት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሶስት ብር 52)

ሚያዚያ  30  ቀን 2018 .

ጠዋት 330-5:00

 

ጠዋት 5:00-5:50

 

የሐራጅ ደንቦች፡-
 

  1. ተጫራቾች የንብረቱን የመነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) የጨረታ ማስከበሪያ በዘመን ባንክ አ.ማ ስም የተዘጋጀ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
  2. አሸናፊው/ዋ የሚለየው በደብዳቤ ሲገለጽ ነው፡፡ አሸናፊው/ዋ አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ አጠቃለው መክፈል አለባቸው፡፡ ይህንን ካላደረጉ ያስያዙት ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ እንደገና ጨረታው ይካሄዳል፣ የዋጋ መቀነስ ከተከሰተ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ልዩነቱን የመጀመሪያው አሸናፊ እንዲከፍሉ ይጠየቃሉ።
  3. ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው።
  4. ንብረቱን አስመልክቶ ማንኛውንም ለመንግስት ሊከፈል የሚገባውን ክፍያ የንብረት ግብር፣ የቤት ማህበር መዋጮ፣ ውዝፍ ሊዝ ክፍያ፣ የአከራይ ተከራይ ግብር፣ ሌሎች ያልተከፈሉ ክፍያዎች ወዘተ (ካሉ) እነዚህን ክፍያዎች በሙሉ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል።
  5. የሐራጅ ሂደቱ ከተጀመረ በኃላ ማንም ተጫራች መውጣት እና መግባት አይፈቀድም፣ ተጫራቹ ሳይፈቀድለት ማናቸውንም ዓይነት ንግግር ማድረግ አይችልም፡፡ ይህንን ደንብ የማያከብር እና ጨረታውን የሚያውክ ተጫራች ካለ እንዲወጣ ተደርጎ ጨረታው በቀሩት ተጫራቾች ይቀጥላል።
  6. የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና ሥነ-ሥርአት ለሚያሟሉ ተጫራቾች የንብረቱን የሐራጅ መነሻ ዋጋውን መጠን በከፊል የሚሸፍን ብድር ባንኩ ሊያመቻች ይችላል፡፡ ባንኩ ብድሩን በማናቸውም ሁኔታ ለአሸናፊው ባይፈቀድ/ባይሰጥ አሸናፊው በዚህ የሐራጅ ደንብ ተ.ቁ 2 ላይ ያለውን ግዴታ እና የተቀሩት ግዴታዎችን ቀሪ አያደርግላቸውም።
  7. ባንኩ ንብረቱን በገዥው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡ ከስም ዝውውር ጋር ያሉ ማናቸውንም ክፍያዎች ገዥው ይከፍላል።
  8. የሐራጅ ሽያጩ የሚከናወነው ሰንጋ ተራ በሚገኘው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 18ኛ ፎቅ ላይ ነው።
  9. ባንኩ በሚያወጣው የጉብኝት ፕሮግራም መሰረት ተጫራቾች የሚሸጠውን ቤት መጎብኘት ይችላሉ።
  10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-6-68 62 16 ወይም 0911152490 ወይም 0911456203 ወይም 0919 60 26 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
  11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ዘመን ባንክ አ.ማ
Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Bid closing time: 11:50
  • Bid opening: 2026-05-08 11:50
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Zemen Bank S.C.
  • Buyer TIN: 0004608547
  • Buyer address: Josef Tito Street
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T12:18:35.000Z
  • Buyer website: https://www.zemenbank.com

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders