የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት ልዩ ልዩ የቦንዳ አልባሳት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት ልዩ ልዩ የቦንዳ አልባሳት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም

1. ማንኛዉም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተጠቀሰዉ አልባሳት በሚገኝበት አድራሻ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 11 የቤ ቁ 1188 ወደ ወሰን በሚወስደው መንገድ ሂል ሳይድ ት/ ቤት ፊት ለፊት በድልድዩ አጠገብ በሚያስገባዉ የመጀመሪያዉ የኮብል መንገድ 200 ሜትር ያክል ገባ ብሎ በሚገኘዉ የድርጅቱ ዕቃ መጋዘን ዉስጥ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት መመልከት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) አሰርተዉ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ማንኛዉም ባንክ ለባንክ ዝዉዉር የሚፈጸም ክፍያ ተጫራች የሚያስተላልፈዉ ገንዘብ በስሙ ከተከፈተ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ብቻ መሆን አለበት።

3. የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ለአሸናፊው ከሚከፈለዉ ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታ ዉጤት በፀደቀ በሶስት(3) ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ይመለስላቸዋል።

4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘዉ ሰነድ ላይ ተጫራቹ የስጠዉ ዋጋ በሚለዉ አምድ /Column/ ስር በቦንዳና በማዳበርያ የሚገዙበትን የነጠላ እና የጠቅላላ ዋጋ እንዲሁም የጠቅላላውን አልባሳት ድምር ዋጋ በአሀዝ እና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀዉ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ሾላ ገበያ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።

5. ተጫራቾች ጨረታዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ የጨረታዉን ሰነድ ማስገባት አለባቸዉ። በአምስተኛዉ ቀን ግን የጨረታ ሰነዱ የሚገባዉ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነዉ።

6. በአምስተኛዉ ቀን የሳምንቱ ቅዳሜ እና እሁድ ላይ የሚዉል ከሆነ ቀጥሎ ባሚውለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

7. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታዉን ማሸነፋቸዉ ከተገለፀላቸዉ ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ ማድረግ አንዲሁም በ3 (ሶስት) ተከታታይ ቀናት ዉስጥ የቦንዳ አልባሳቱን የመረከብ እና የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ ይህ ካልሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።

8. ተጫራቾች የቦንዳ አልባሳት የጨረታ ሰነድ እና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ /ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በድርጅቱ የንግድ ሂሳብ ቁጥር 1000001819023 (Integrated Family Service Organization) በማስገባት ዋናዉን ደረሰኝ ይዘዉ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት እስከ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአምስተኛዉ ቀን 4፡00 ሰዓት የሰነዱ ሽያጭ ይጠናቀቃል።

9. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታዉ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአምስተኛዉ የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያዉ ቀን በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

10. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያያዘዉ የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

11.ድርጅቱ ስለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-11-66-65-64 መደወል ይችላሉ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-10
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስተኛዉ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-10 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአምስተኛዉ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Integrated Family Service Organization
  • Bid bond: 20%
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T12:25:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders