ፒናክል ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ንብረት የሆኑትን 6 (ስድስት) ያገለገሉ የጭነት መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ፒናክል ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ንብረት የሆኑትን 6 (ስድስት) ያገለገሉ የጭነት መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በሚካሄድበት ቀን መኪናዎቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት በጨረታው ተወዳድሮ መኪናዎቹን መግዛት ይችላል።
የመኪናዎቹ አጠቃላይ መረጃ፤
|
ተ.ቁ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሽከርካሪ አይነት |
የመጫን አቅም |
የሞተር ቁጥር |
የቻንሲ ቁጥር |
የጨረታው መነሻ ዋጋ |
|
1 |
3-A08976 |
ቻይና ሲኖ ትራክ ደረቅ ጭነት (2021) |
148 ኩንታል |
WD615.47210 107022807 |
LZZ5BLSF2 MN764833 |
8,885,000.00 |
|
2 |
3-A08973 |
ቻይና ሲኖ ትራክ ደረቅ ጭነት (2021) |
148 ኩንታል |
WD615.47*210 107022697* |
LZZ5BLSF0 MN764832 |
8,885,000.00 |
|
3 |
3-A08940 |
ቻይና ሲኖ ትራክ ደረቅ ጭነት (2021) |
148 ኩንታል |
WD615.47210 107016707 |
LZZ5BLSF9 MN764828 |
8,885,000.00 |
|
4 |
3-B14210 |
ኢቸር ቫን (2019) |
48 ኩንታል |
E423CDKK302676 |
MC2E1GLC OKK451682 |
3,945,000.00 |
|
5 |
3-B14214 |
ኢቸር ቫን (2019) |
48 ኩንታል |
E423CDKK303916 |
MC2E1GLC OKK451687 |
3,945,000.00 |
|
6 |
3-B14179 |
ኢቸር ቫን (2019) |
48 ኩንታል |
E423CDKK304014 |
MC2E1GLC OKK451700 |
3,945,000.00 |
የተጫራቾች መመሪያ
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቦሌ ላኪ ህንጻ 7ተኛ ፎቅ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ መኪናዎቹን ለመግዛት የገለጹትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ፒናክል ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር ስም በማሰራት እና የሚገዙበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ለውድድር አይቀርብም።
3. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ማየት ይችላሉ።
4. ጨረታው ሚያዝያ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ሚያዝያ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾት ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቦሌ ላኪ ህንጻ 7ተኛ ፎቅ ይከፈታል:: ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።
5. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ሙሉ ክፍያ ከፍሎ ዕቃውን መረከብ ይኖርበታል።
6. በጨረታው ተሳትፈው ላላሻነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የጨረታው አሸናፊ ለስም ማዛወሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎችን በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ: በ 09 44 30 91 99 / 09 44 73 50 43 / 09 03 33 02 33 በመደወል መጠየቅ ይቻላል
Tender details
- Deadline: 2026-04-16
- Bid closing time: 16:00
- Bid opening: 2026-04-17 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Pinnacle Trading Share Company
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 05, 2026
- Posted at: 2026-04-06T13:40:46.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.