አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አቢሲንያ ባንክ /አ.ማ/ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዛቸውንና በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) መሠረት ንብረቶቹ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ (አ.ማ) ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል።
- ተበዳሪው /መያዣ ሰጪው/ በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፣ ግብር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል፡፡ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ለቀሪው የሊዝ ክፍያ ገዢው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ይዋዋላል።
- ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል።
- ከታች በሰንጠረዥ ውስጥ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱ ንብረቶች በሀራጅ ሲሸጡ በባንኩ የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟላ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢ /አሸናፊ/ ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል፡፡
- ከታች በሰንጠረዥ ውስጥ በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሰው ንብረት በሀራጅ ሊሸጥ ለገዥው ከፊል ፋይናንስ /ብድር/ ባንካችን የማይሰጥ ስለሆነ በካሽ ክፍያ ብቻ ግብይት እንደሚፈጸም እንገልጻለን፡፡
- ከታች በሰንጠረዥ ውስጥ በተራ ቁጥር 3 የተጠቀሰው ንብረት ከኤስ.ዲ.ፒ (SPECIAL DEVELOPMENT PLAN) ፕላን ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ የኮርደር ልማት በግንባታ ላይ ያለውን ህንፃ የማይነካ ሲሆንለ የተገነባውን መጋዘን ግን በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 3 (ሶስት) ሜትር የሚነካው መሆኑን ከሸገር ገላን ክ/ከተማ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት የቀረበው መረጃ ያሳያል፡፡
- የጨረታው ቦታ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ለገሀር በሚገኘው የአቢሲንያ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት 4ኛ ፎቅ የፎርክሎዠር እና ዴት ሊቲጌሽን ለጨረታ ባዘጋጀው ቢሮ ላይ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 15 11 53 እና 0115 15 07 አአ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቱ አይነት እና አገልግሎት |
የቦታው ስፋት በካሜ |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀን |
የምዝገባ ሰዓት |
የጨረታ ሰዓት
|
ጨረታው የወጣበት ጊዜ |
|
1 |
ይክመኤል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የገግ/ማህበር |
አቶ ጸጋዬ ባህሩ ገበየሁ |
የኢንዱስትሪ ህንጻ/መጋዘን / |
7590.532 |
ደብኢፓ/03/0250/2016 |
አማራ ብ/ክ/መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረብርሃን ከተማ ጫጫ ክ/ከተማ |
34,750,446.47 |
ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም. |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
በድጋሚ |
|
2 |
አቶ ይረገም ተፈረ አወቀ |
አቶ ሰለሞን መኮንን አድማሱ እና ወይ. ወላማዊት ዮሴፍ |
መኖሪያ ቤት |
457 |
የካ/200985/09 |
አዲስ አበባ ከተማ የካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 |
8,413,484.13 |
ግንቦት 05 ቀን 2018 ዓ.ም. |
8፡30-9፡30 |
9፡30-10፡00 |
ለመጀመሪያ ጊዜ |
|
3
|
ቤክፋም ጠቅላላ ንግድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አቶ በረከት ክፍል ባህታ |
ግንባታው ያልተጠናቀቀ ለንግድ የሚሆን ህንጻና መጋዘን |
2500 |
022622/1 |
በቀድሞ አዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በአሁኑ ኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ገላን ክ/ከተማ |
28,233,809.58 |
ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም. |
4፡30-5፡30 |
5፡30-6፡00 |
በድጋሚ |
|
አቶ በረከት ከፈን ባህታ |
Tender details
- Deadline: 2026-05-14
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-14 12:00
- Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
- Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 05, 2026
- Posted at: 2026-04-06T14:22:32.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.