በጉ/ክ/ከ አዲስ ተስፋ የመ/ደረጃ እና የካቲት 12 ቅ/መ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ የጥገና ስራዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 003/2018
በጉ/ክ/ከ አዲስ ተስፋ የመ/ደረጃ እና የካቲት 12 ቅ/መ/ደ/ት/ቤት የ2018 ዓ.ም በጀት አመት ሶስተኛ ዙር በውስጥ ገቢ አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የጥገና ስራዎች በሎት ከፋፍሎ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዘርፉ ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
ጥገና ስራዎች |
2% የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን |
|
ሎት-1 |
የመምራን ሎከር ጥገና የመሪት ሊሻ የማድረግ ስራ |
|
1. የሚወዳደሩበትን የሎት አይነት ተዛማጅ የሆነ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይና ጨረታ ለመሳተፍ የተፈቀደበትና የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ኮፒ በጨረታ ሰነድ በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200 ብር/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ሽሮ ሜዳ በሚገኘው አዲስ ተስፋ የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 በመምጣት ወይም ወኪሎቻቸውን በመላክ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
3. ጥገናዎች ዋጋ 15 ፐርሰንት ቫት ተጨምሮ ይቅረብ፡፡ ባይቀርብ እንደተጨመረ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ መሙላት አለባቹ።
5. የምታስገቧቸው ሰነዶች ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም፡፡ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡ ፡ ጥቃቅን እና አነስተኛ እቃ አቅራቢዎች በሚመለከተው አካል በትምሀርት ቤቱ ስም አድራሻ የተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከጠዋት 2፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን በስም የታሸገ ፖስታ በቢሮ ቁጥር 5 ማስገባት ይችላሉ።
8. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ5ኛው ቀን ከምሽት 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ በንጋታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በተገኘው ሰው ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል።
9. አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበረ ማቅረብ አለባቸው።
10. አሸናፊው ያሸነፈባቸው ጥገናዎች ከነሙሉ ማቲሪያሉ እዲሰራ እንደ አስፈላጊነቱ መጨመርና መቀነስ ይችላል።
11 ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ሽሮሜዳ 31 ቁጥር አውቶብስ ማዞሪያ ወደ ኪዳነ ምህረት መሄጃ መንገድ 50 ሜትር ገባ ብሎ በጉስሴ ክፍስ ከተማ ትም/ፅ/ቤት አዲስ ተስፋ የመጀ/ደ/ት/ቤት ስልክ ቁጥር – 0111-54-55-13
በጉ/ክ/ከ አዲስ ተስፋ የመ/ደረጃ እና የካቲት 12 ቅ/መ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-11
- Bid closing time: 16:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በ5ኛው ቀን 10፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-12 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በ5ኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ተዘግቶ በንጋታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yekatit 12 Primary School
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 07, 2026
- Posted at: 2026-04-07T08:33:34.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.