ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን የፅሕፈት መሣሪያዎች፣ የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ቀለም (ቶነር) እና የሕንፃ መሣሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሠነድ ቁጥር- ልዲቁኮ 13/2018
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተጠቀሱ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፣
- የፅሕፈት መሣሪያዎች
- የፕሪንተር እና የፎቶ ኮፒ ማሽን ቀለም (ቶነር)
- የሕንፃ መሣሪያዎች
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የዘመኑን የግብር ግዴታ ስለመወጣታቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 07 በመቅረብ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ጨረታ መዝጊያ ቀን ድረስ መግዛት ይችላሉ።
3. ጨረታው ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ለመገኘት የቻሉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባለበት ይከፈታል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በሲፒኦ ወይም እንደተጠየቀ ወዲያውኑ በሚከፈል የባንክ ጋራንቲ በፖስታ አሽገው እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀንና ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 08 ማቅረብ ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
5. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ-ስልክ ቁጥር 058-218-02-73 ሞባይል 09-18-08-5589/09- 96-14-20-56 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-05-50/60 በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ልህቀት የዲዛይንና ቁጥጥር ኮርፖሬሽን፡
ባህርዳር-ኢትዮጵያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-04-24 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Excellence Design and Supervision Corporation
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 07, 2026
- Posted at: 2026-04-07T09:02:52.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.