Stationery and office consumables
ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ የ2018/19 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ሰነድ ቁጥር፡- ዘኢአማ/7/017/2018ዓም
ዘመን ኢንሹራንስ አ.ማ የ2018/19 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፦
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
|
ምድብ 1 |
የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች (Different items of stationery) |
|
ምድብ 2 |
የተለያዩ የህትመት ውጤቶች (Different items of printing) |
|
ምድብ 3 |
የደንብ ልብስ (Uniform) |
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራቾች (አቅራቢወች)መወዳደር ይችላሉ።
1. በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር Tine number/ ያላቸዉ
3. በአቅራቢነት ዝርዝር ዉስጥ (Supply list)የተመዘገቡ በጨረታ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸዉ።
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስት ወይም (CPO) ማቅረብ አለባቸዉ።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለበት ካልተገለጸ የቀረበዉ ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን እንደሚያካትት ተደርጎ ይወሰዳል።
7. ተጫራቾች በቢሮዉ የተዘጋጀዉን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ሰነድ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ዉስጥ በኩባንያዉ ዋናዉ መስሪያ ቤት ቦሌ አለም ህንጻ 2ኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 2፡00 እስክ ቀኑ 11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በኩባንያዉ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
8. ማንኛዉም ተጫራች የሚጫረትበትን ዕቃ በየምድቡ የጠቅላላ ዋጋዉን ብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ) በዘመን ኢንሹራንስ አማ ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/CPO/ ማስያዝ ይጠበቅበታል።
9. ማንኛዉም ተጫራች የሚያስገቡት ዋጋ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ካለዉ ተቀባይነት አይኖረዉም።
10. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት ተለይቶ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ መቅረብ አለበት። ማንኛዉም ተጫራች በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጂቱ ማህተም እና ፊርማ ያረፈበት የጨረታ ሰነድ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ።
11.የጨረታ መዝጊያ ቀን ነሐሴ 13/2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል።
12. ጨረታዉ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል።
13.ኩባንያዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
14 ኩባንያዉ ከአሸናፊዉ ድርጅት ላይ የዕቃ ብዛት በቀረበዉ ዋጋ መስረት 20% መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
15. በዕለቱ ጨረታዉ የሚከፈተዉ እንደየምድቡ ቅደም ተከተል መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ 011 615 1493 ወይም በአካል ዘመን ኢንሹራንስ ዋናዉ መስሪያ ቤት ቦሌ አለም ህነጻ 5ኛ ፎቅ በመምጣት መሉ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-19 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Zemen Insurance S.C.
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T14:02:41.000Z