Stationery and office consumables

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የምግብ አቅርቦት እና አላቂ የቢሮ እቃ በሎት የተዘረዘሩ ግዥዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2019 በጀት ዓመት የምግብ አቅርቦት እና አላቂ የቢሮ እቃ በሎት የተዘረዘሩ ግዥዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1. የምግብ አቅርቦት ግዥ ለ60 ስፖርተኞች የሚሆን
  • ሎች 2. የቢሮ አላቂ ዕቃ ዓይነት በጨረታ ሰነድ መሠረት

በመሆኑም ተጫራቾች፣

1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፣

5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ሎት 1 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ሎት 2 5000 /አምስት ሺህ ብር / በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ጨረታው በአንድ ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ በድርጅቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ሲሆን እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ4፡00 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና፣ ፊርማቸውን፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው፣

7. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የግዥውን ብዛት/ መጠን/ እንደአስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ / ለመጨመር / መብቱ የተጠበቀ ነው፣

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የምግብ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው የምግብ ሜኑ ዝርዝር መሠረት እና የቢሮ አላቂ ዕቃ የጨረታ ሰነድ መሰረት ብቻ ነው መወዳደር የምትችሉት።

9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 221 6730 / 09 16 15 59 30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የመ/ቤቱ አድራሻ ከሀዋሳ ሲዳማ ክልል በቀድሞ ፖሊስ ኮምሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ።

የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ቀን
  • Bid opening: 2026-08-25 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ሲሆን እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ4፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: Sidama Region Sport Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T12:40:11.000Z
← Back to all tenders