በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የተለያዩ እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
የግዥ መለያ ቁጥር 003/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የሚከተሉትን እቃዎች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት አንድ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
- ሎት ሁለት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች/ቴሌቪዥን
- ሎት ሶስት የኮምፒዉተር እና የቢሮ ጥገና/Maintenance tool Kit
- ሎት አራት፡-የተለያዩ የኮምፒዉተር ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና እንዲሁም የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ከሚወዳደሩበት ዕቃ ወይንም አገልግሎት ግዥ ጋር ለመወዳደር ተያያዥነት ያለዉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃዎችን (ክሊራንስ) ከግብር አስገቢው መ/ቤት ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት ግዥ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ለተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT )የተመዘገቡ መሆኑን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ሰርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የአገር ውስጥ የድጋፍ አቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት(በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት) የተደራጁ መሆኑን እና ከአደራጃቸዉ አካል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለአጠቃላይ ከሎት አንድ እስከ ሎት አራት ለእያንዳንዳቸዉ ሎቶች የአጠቃላይ ዋጋ 5000 ብር በባንክ በተመሰከረለት (CPO)ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ CPO መሰራት ያለበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ለአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ዕ/ቤት በሚል አድራሻ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ መክፈቻው ቀን ድረስ ሳሊተ ምህረት ቤ/ክርስቲያን ፊትለፊት ሜሪዲያን ህንፃ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከግዥ ቡድን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ:: የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያጠቃለለ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከ11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀዉ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይገባቸዋል::ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በመ/ቤቱ አዳራሽ 2ተኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል::እያንዳንዱ ተጫራች ለጨረታ ለመወዳደር በሚቀርብበት ወቅት ፋይናንሻ እና ቴከኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር/ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ኮፒ እና ኦርጅናል ተለይቶ በፖስታዉ ዉጫዊ ገጽ መጻፍ አለበት።
- ሰነዱን በሚመልስበት ወቅት ስልጣን ባለው አካል መፈረምና የድርጅቱ ማህተም መደረግ አለበት ነገር ግን የሚፈርመው አካል ተወካይ ከሆነ የውክልና ማስረጃ መያያዝ አለበት።
- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- የጨረታው አሸናፊ የአሸናፊነት ደብዳቤ እንደደረሰዉ የዉሉን ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) CPO በዉል ማስከበሪያነት በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
- ተጫራቾች በሚወዳደሩባቸው ሁሉም ዕቃዎች ላይ የጨረታ ሰነዱን ሲያስገቡ ናሙናዎችንም ለንብረት አስተዳደር ክፍል ማስረከብ አለባቸው።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታዉ ከተከፈተበት ጀምሮ ለ90 ቀናት መቆየት አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
ስልክ ቁጥር 01116731504
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
ለአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-04-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-17 10:30
- Bid opening (note): የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
- Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 07, 2026
- Posted at: 2026-04-07T09:11:21.000Z
Documents
Categories
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurnitureComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Machines and ComputersMaintenance and RepairHand Tools and Workshop EquipmentMechanicalCleaning and Janitorial Equipment and ServiceAmharic2merkatoአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 3 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤትAddis Ababa
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.