የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለምዕ/ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ለደም ባንክ አገልግሎት የሚውል ግንባታ ደረጃ 5 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ለምዕ/ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ለደም ባንክ አገልግሎት የሚውል ግንባታ ደረጃ 5 ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) እና ደረጃቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ /cash payment order/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ ስም በማሰራት ዋጋ ከሞሉት የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት (bill of quantity) በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ነው፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ከገንዘብ ያዥ ከግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን የቴክኒክ እና የፋይናንስ ብሎ በመለየት በተለያየ ፖስታ በማድረግ በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ምዕ/ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው በ31ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/መምሪያ በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
10.ተጫራቾች የዋጋ ቅናሽ ወይም Rebate ማሰቀመጥ ከፈለጉ በዋጋ መሙያው ማጠቃለያ ላይ በተቀመጠው መሰረት በፐርሰንት ማሰቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በምዕ/ጎጃም/ገንዘብ መምሪያ ስም ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
12.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13.ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ31ኛው ቀን በ3፡30
- Bid opening: 2026-05-06 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ31ኛው ቀን በ4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: West Gojam Zone Finance and Economic Corporative Command
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 06, 2026
- Posted at: 2026-04-07T10:43:42.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.