የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት በባህርዳር አለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ የሚገኙ 12 (አስራ ሁለት) ለተለያዩ አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል

Description

የቦታ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡ - SSNT-T610

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት በባህርዳር አለም አቀፍ አየር ማረፊያ እና በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ የሚገኙ 12 (አስራ ሁለት) ለተለያዩ አገልግሎት መስጫ የሚውሉ ባዶ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል።

በባህርዳር አስም አቀፍ አየር ማረፊያ፡- ካፊቴሪያ እና ሬስቶራንት፣ የባህል አልባሳት እና የጌጣጌጥ ሱቅ ፣ ሚኒማርኬት ሱቅ እና የመረጃ ዴስከ።

በኮምቦልቻ አየር ማረፊያ፡- ካፊቴሪያ እና ሬስቶራንት እና የልጆች የመዝናኛ እና ካፊቴሪያ)።

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ለማቅረብ ፈቃደኛ እንዲሁም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡-

  1. ህጋዊና የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፤ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ረቡዕ ሚያዝያ 28 ቀን 2018ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ባሉት ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNTT610 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ቅጂውን (scan copy) ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
  3. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ለእያንዳንዱ የቦታ ኮድ ጨረታ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት የሚያገለግል የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለበት። ከኢንሹራንስ እና ቅደመ ሁኔታ ያለው ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
  4. ተጫራቾች ህጋዊ ሰነዶቻቸውን (የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የTIN እና የቫት ሰርተፊኬት) እና የመወዳደሪያ ፋይናንሽያል ፕሮፖዛል ዋናውን በአንድ ኤንቨሎፕ እና ኮፒውን በሌላ ኤንቨሎፕ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በሌላ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማሸግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መስሪያ ቤት ውስጥ በሚገኘው ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል እስከ ረቡዕ ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ያዕቆብ መስቀላ: በስልክ ቁጥር፡ +251-11 517-8025 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

ኢሜል: YaikobM@ethiopianairlines.com 

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-06
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid opening: 2026-05-06 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ የቦታ ኮድ ጨረታ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Apr 08, 2026
  • Posted at: 2026-04-08T09:42:58.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders