Office and commercial space rental
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል
Description
የሱቅ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡-EMC/OT/IHBD/SHOPRENT/01/2019
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን በዋናው መስሪያ ቤት የሚገኙ ሱቆችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
ሱቁ የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታው መዝጊያ
|
የጨረታው መክፈቻ |
ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
አ.አ ዋናው መስሪያ ቤት |
||||
|
1 |
የተለያዩ መጠን (size) ያላቸውን ሱቆች |
3 |
አዲስ አበባ
|
21/12/2018 ዓ.ም
|
4፡00 ጠዋት
|
21/12/2018 ዓ.ም
|
4፡30 ጠዋት |
|
ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች (መመሪያዎች) ፡-
- የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ብሎክ 2፣ በሚገኘው የኮርፖሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በግንባር በመገኘት የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል በሶፍት ኮፒ ( soft copy ) መግዛት ይችላሉ፤
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለኪራይ የተዘጋጁትን ሱቆች ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታውን ለመክፈት አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ሱቆች በሚገኙበት ቦታዎች በአካል በመገኘት ኮርፖሬሽኑ በሚመድበው ሰራተኛ አስጎብኚነት መመልከት ይችላል፡፡ የሱቆቹ ብዛት እንደአስፈላነቱ ቁጥሩ ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች ብር 20000.00 (ሃያ ሺ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሣጥኑ ውስጥ ከሰነዳቸው ጋር የማስገባት ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡አሸናፊ ለሆኑትና ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ህጋዊ ባንክ ከሆነ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ሊታሰብላቸው ይችላል ወይም ለተሸነፉት ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊዎች ለሱቅ ኪራይ ቅድሚያ የሶስት ወራት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በላዩ ላይ ድርጅቶች ከሆኑ ማህተም ያረፈበት፣ የግለሰቦች ከሆኑ ደግሞ ሶስት ፊርማ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀንን በተመለከተ ከላይ በሰንጠረዥ ዋናው መ/ቤት በተገለጸው ቀን እና ሰዓት መሰረት ከጠዋቱ በ4፡00 ታሽጎ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 በዋናው መ/ቤት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለሚከራዩት ሱቆች ስፋት ካሬ ሜትር ዋጋ በቁጥርና በፊደል ስርዝ ድልዝ የሌለበት በግልጽ ሞልተው በታሸገው ኤንቬሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋ ማስቀመጥ የሚኖርባቸው ሲሆን ገዥ የሚሆነው የነጠላ ዋጋው ይሆናል፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0911622263 /ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡
- ኮርፖሬሽነ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተከራዮች ሱቆችን ለጌጣጌጥ፣ ለማእደን ውጤቶች፣ ለባህላዊ አላባሳት እና ቅርጻቅርጾች መሸጫ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎት የሚከራዩ ይሆናል፡፡ ከአልኮል መጠጥ ውጭ፡፡
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
+251-0911622263
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-27 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Mineral Corporation (EMC)
- Buyer address: 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T08:57:28.000Z