Office and commercial space rental

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል

Description

1ኛ ዙር የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር፡- አ/ከ/ክ/ከ/ወረዳ 12 ፋይናንስ ግዢ/ዋ/ስ/ሂ/የጨ/ቁ-002/2019

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት 1ኛ ዙር ለሚያከናውነው አጠቃላይ የአላቂ እቃ እንዲሁም አገልግሎት ግዥ የዝግጅት ምዕራፉን አጠናቆ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የእቃና አገልግሎት ግዥ መደቦች ላይ ተቋሙ ያስቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ለውድድር ይጋብዛል።

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያና አላቂ እቃዎች.................….CPO (2%)
  • ሎት 2.የፅዳት እቃዎች..........................................CPO (2%)
  • ሎት 3.የደንብ ልብስ........................................................... CPO (2%)
  • ሎት 4.ቋሚ እቃዎች.......................................... CPO (2%)
  • ሎት 5.የሰራተኛ ምገባ.....…………………………………. CPO (2%)
  • ሎት 6.የመኪና ጎማ እና እቃዎች……………………………………. CPO (2%)
  • ሎት 7 የስፖርት እቃዎች………………………………………CPO (2%)
  • ሎት 8.ዲኮር....................................................... CPO 10,000.00
  • ሎት 9.መስተንግዶ………………………..…………………… CPO 10,000.00
  • ሎት10.ትራንስፖርት…………………………………………. CPO 10,000.00
  • ሎት11. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና……………………………….. CPO 10,000.00
  • ሎት 12 ፈርኒቸር ጥገና……………………………………….. CPO 10,000.00
  • ሎት 13.የህትመት ስራዎች……………………………………………..…. CPO 10,000.00
  • ሎት 14 የግብርና ግብአት እቃዎች…………………………… CPO 10,000.00
  • ሎት 15.የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት……………………………. CPO 10,000.00

መስሪያ ቤታችን ከላይ በተገለፀው የግዥ መደብ መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ወይም አቅራቢን አወዳድሮ ግዥውን ለመፈፀም ይፈልጋል።

በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው

2. የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃና የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው

3. የዘመኑን ግብር የከፈለበት ክሊራንስና ህጋዊ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው

4. የጨረታ ሰነዱ ሙሉ እያንዳንዱ ገፅ ተሞልቶ ተፈርሞ ማህተም ተደርጎበት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መመለስ አለበት /ይህን ሳያደርግ የጨረታ ሰነዱን ለሚመልስ ነጋዴ ከጨረታው ውድድር ውጪ እንደሚሆኑ እናሳውቃለን።

ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ኮልፌ አጠና ተራ መናፈሻ ፊት ለፊት የተቋሙ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 101 በሚገኘው ፋይናንስ ፅ/ቤት በግንባር በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300.00ብር (ለአንድ ሎት) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል ከላይ በተገለፀው መሰረት ከሎት 1-7 የሚያቀርቡትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% እንዲሁም ከሎት 8-14 ደግሞ 10000.00 /አስር ሺ ብር/ ህጋዊ CPO በተቋማችን ስም አስርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመዋዋላቸው በፊት ያሸነፉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ህጋዊ CPO በማሰራት ለጨረታ ውል ማስከበሪያነት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም የጨረታ ሰነዱን ሙሉውን በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናልና ኮፒ ብለው በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጫራች የሚሞላውን ክፍል በጠቅላላ ሞልተው ፈርመው ማህተም አድርገው የጨረታ መቀበያ ቀነ ገደቡ ሳያልፍ ለዚሁ ስራ ተብሎ በፅ/ቤቱ ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት የመጠቀሚያ ጊዜው ቢያንስ 1 ዓመትና ከዛ በላይ የሆነ እና በሳምፕሉ መሰረት አድርገው ወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

በተጨማሪም ለጥቃቅንና አንስተኛ ተወዳዳሪዮች የጨረታ ማስከበርያ አስተያየት የምናደርገው ለሚያመርቱት ምርት ብቻ እሱንም በደብዳቤ የምናስተናግድ መሆነ እንገልፃለን፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም እረፍት ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን በትህትና እንገልፃለን።

አድራሻ፡- ኮልፌ አጠና ተራ ኮልፌ ፓርክ ፈት ለፊት ወይም ቁጠባ ሰፈር ጀርባ ወደ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን/ሎሚ ሜዳ በሚወስደው መንገድ 200 ሜ. ወደ ግራ ገባ ብሎ

ለበለጠ መረጃ በ0118 278 077 / 0910 584 301 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ፋይናንስ ፅ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-08-21 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Sub City Woreda 12 Finance Office
  • Buyer address: ኮልፌ አጠና ተራ ኮልፌ ፓርክ ፊት ለፊት ወይም ቁጠባ ሰፈር ጀርባ ወደ ፊሊጶስ ቤተከርስቲያን/ሎሚ ሜዳ በሚወስደው መንገድ 200 ሜ ወደ ግራ ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለአንድ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T12:58:08.000Z
← Back to all tenders