Office and commercial space rental
በቦሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ለንግድ ቤት የሚሆኑ የተለያዩ ሱቆች አገልግሎት የሚውል አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ስፖርት ም/ቤት 01/2018
በቦሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት በወረዳ 14 ለሚ ሜዳ የሚገኘውን G+1 ለንግድ ቤት የሚሆኑ የተለያዩ ሱቆች አገልግሎት የሚውል አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
በመሆኑም ቤቶቹ የምድር ቤትና G+1 ያለው ሲሆን፣ 20 የተለያዩ ሱቆች ሲሆኑ የተሟላ ሽንት ቤት፣ ውኃና መብራት እንዲሁም ጥበቃ ያለው መሆኑን እናሳውቃለን። ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
1. የታደሰ የቀበሌ/ የነዋሪነት/ መታወቂያ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱ የተገዛበት ወይም የተከፈለበት ገቢ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒ አብሮ ከጨረታ ሰነዱ ጋር መያያዝ ማስገባት/ ይኖርበታል።
2 ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) “በቦሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት በስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች” ስም በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በቦሌ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደር እና ፋይናነስ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ የቦሌ ክ/ከተማ ህንፃ ላይ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በስፖርት ማዘዉተሪያ ስፍራ አካውንት ቁጥር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000757608603 በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ግዥ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. በተጫራቹ የተሞላው ዋጋ በግልጽ ፅሑፍ መቀመጥ እና መፈረም አለበት።
6. አንድ ተጫራች መጫረት የሚችለው ለአንድ (1) ሱቅ ብቻ ነው። ይህን ተላልፎ የተገኘ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል። የተጫረተውን ሱቅ ካሸነፈ በኋላ ውል ሳይዋዋል ቢቀር ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ይወረሳል።
7. አሸናፊ አካላት ሱቆቹ ለመጠጥና ከመጠጥ ጋር የተያያዙ ንግዶችን፣ ለብረታ ብረት ብየዳ ስራ፣ ለቁማር (ቤቲንግ)፣ ለአልኮል፣ ለጫትና ሲጋራ እንዲሁም አካባቢን በድምጽ የሚረብሹ ነገሮች መጠቀም ክልክል ነው።
8. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ይሆናል። ማናቸውም ተጫራቶች በአንድ ቤት ላይ እኩል ዋጋ ካላቀረቡ እና ከመካከላቸው አንድ ሴት ተጨራች ካለች አሸናፊ እንድትሆን ይደረጋል፤ ሆኖም እኩል ዋጋ ያቀረቡት ተጫራቶች ተመሳሳይ ጾታ ከሆኑ አሸናፊው በጨረታ ኮሚቴ አባላት ፊት ቀርቦ በዕጣ የሚለይ ይሆናል። ይሁን እንጂ በዚህ ሂደት አሸናፊ የሆነው ተጫራች በጊዜ ገደቡ ቀርቦ ካልተዋዋለ ለቦታው ሁለተኛ የወጣው ተጫራች ጽ/ቤቱ በሚያስቀምጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ መዋዋል ይችልል።
9. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ካልሆነ ግን በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቦሌ ክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፑል አስተዳደር እና ፋይናነስ ጽ/ቤት መገናኛ አደባባይ 3ተኛ ፎቅ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ የዲዛይን ስራዎች ፑል አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-20 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ በመጨረሻው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ የስራ ቀን ከሆነ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ካልሆነ ግን በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Bole Sub City Administration Design and Construction Works Bureau
- Buyer address: መገናኛ አካባቢ የሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት ሁለተኛ ወለል
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ጥቅል 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Lessan (Aug 08, 2026)
- Posted at: 2026-08-08T09:00:33.000Z