Office and commercial space rental

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት

  • ሎት1 የአላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት 2. የጽዳት እቃዎች
  • ሎት3. የደንብ ልብስ እቃዎች
  • ሎት 4 የህትመት ዉጤቶች
  • ሎት 5. የመስተንግዶ አገልግሎቶች
  • ሎት 6. የመኪና እቃዎች
  • ሎት 7. የትራንስፖርት አገልግሎት.

ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸዉ።

1. ተጫራቾች በዘርፋ የተሰማሩበት ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

3. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዘገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O ማቅረብ አለባቸው።

ሎት ቁጥር

ሎት ዝርዝር

የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት 1

አላቂ የቢሮ እቃዎች ለሎት 1. አላቂ የቢሮ እቃ

15,000.00ብር

ሎት 2

የጽዳት እቃዎች ለሎት 2. ጽዳት እቃዎች

25,000.00ብር

ሎት 3

የደንብ ልብስ ለሎት 3. ደንብ ልብስ እቃዎች

25,000.00ብር

ሎት 4

የህትመት ውጤቶች ለሎት 4. የህትመት ውጤቶች

10,000.00 ብር

ሎት 5

መስተንግዶ ለሎት 5. መስተንግዶ እቃዎች

5,000.00ብር

ሎት 6

የመኪና እቃዎች ለሎት 6. የመኪና እቃዎች

10,000.00 ብር

ሎት 7

የትራንስፖርት ለሎት 7. የትራንስፖርት

5,000.00 ብር

6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር በመክፍል የተዘጋጀውን ሰነድ ከፋይናንስ ጽ/ቤት ከተቋሙ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አሥር/ተከታታይ የስራ ቀናት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት ይቻላሉ፡፡ በእያንዳንዱ ሰነድ እና መረጃ ላይ ማህተም በመምታት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ኦሪጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ማሸጊያዎች በማሸግ ፖስታው ላይ ኦሪጅናል ብሎ በመጻፍ ኮፒዉን ኮፒ ብሎ በመጻፍ በተጨማሪ ሁለቱንም ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።

10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

11. ተጫራቾች ባሰገቡት ናሙና መሰረት እቃዎች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ሆኑ ካለተገኘ ከናሙና ውጪ ያመጡ ተጫራቾች ንብረታችዉ ሙሉ በሙሉ ተወርሶ ለአስተዳደር ገቢ ይደረጋል።

12. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በ5 ቀናት ውስጥ ለመስረያ ቤቱ በራሱ ትራንስፖርት ማስረከብ ይኖርበታል።

13. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለጨረታ ያሰገቡትን ናሙና 6 ወር ከሞላ ወደ ወረዳዉ አስተዳደር ገቢ ይደረጋል።

16. ወቅታዊ /ወርሃዊ/ የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ለገቢዎች ጽ/ቤት ያሳወቁበትን የሚያረጋግጥ የሰነድ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ከአትላስ ሆቴል ወደ ውሰጥ ገባ ብሎ ሻላ መናፈሻ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0116-63-93-38

ማሳሰቢያ፡- በመጨረሻም የጨረታ ሳጥን የሚገኝበት ቦታ ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-20 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Sub City Administration Woreda 03 Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Lessan (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T08:53:14.000Z
← Back to all tenders