አቢሲንያ ባንክ አ.ማ. የመኖሪያ ቤት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለመጀመሪያ ጊዜ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ አ.ማ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና በሰንጠረዡ የተገለፀውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እንደተሻሻለው ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታና ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በአቢሲንያ ባንክ አማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ እጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ቼክ ወይም ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው/መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ መገኘት ይችላሉ::ነገር ግን ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎችን ገዥ ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ እዳ ደግሞ ወደ አሸናፊው/ገዥው የሚተላለፍ ይሆናል።
  • የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ በሚገኝበት የከተማ አስተዳደር ዘንድ ቀርቦ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን ግብርና ታክስ ይከፍላል።
  • ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዘዋወር ባንኩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
  • የጨረታው አሸናፊ ለመንግስት የሚከፈለውን 15% (አስራ አምስት በመቶ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ለመንግስት የሚከፍለው ጉዳዩ የሚመለከተው የመንግስት አካል መከፈል አለበት ካለ ብቻ ነው።
  • በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • ንብረቱን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ወይም ለማየት የሚቻል ሲሆን፣
  • ጨረታው የሚካሄደው በሰንጠረዡ ላይ ተለይቶ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 022-212-1696 እና በ022-212-0730 አዳማ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

የተበዳሪው ስም

ከተበዳሪው የሚፈለግበት ቀሪ ዕዳ

የመያዣ ሰጪው ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም

የምዝገባ ሰዓት  

የጨረታ ስዓት

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

የንብረቱ

አገልግሎት

 

የቦታው ስፋት (በካ.ሜ)

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

1

አቶ ሁሴን ኤዳኦ ገርጆ

እስከ ታህሳስ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ብር 584,547.36

ወ/ሮ ዘይነባ አብዱልከሪም ጂማ

 

በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/፣ አሰላ ከተማ፣ 13 ቀበሌ

1,023,700.94

 

ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም

 

4:00-4:30

 

4:30-5:30

 

አቢሲንያ ባንክ አሰላ ቅርንጫፍ ውስጥ

 

የመኖሪያ ቤት

 

200.00

19413/97/07

 

ጨረታው ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም ብድሩ ከተከፈለ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-05-12 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bank of Abyssinia S.C.
  • Buyer address: Addis Ababa Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 08, 2026
  • Posted at: 2026-04-08T11:28:08.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders