በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማ እና በዙሪያዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ክ/ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶች እና የሕክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድኃኒት ቤቶች የዱቤ /credit እና የጥሬ ገንዘብ / cash ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግሥት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናችሁ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
1. በንግድ ዘርፍ ወይም በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የቲን ማስረጃዎች
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለ 20 ተከታታይ የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ ) ጉለሌ ክ/ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
3. ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚቻል ሲሆን 4፡30 ሰዓት የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ስለሆነ አርፍዶ የሚመጣ ተቀባይነት የለውም፡፡ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን በድርጅቱ ግዥ ዳይሬክቶሬት ከፍል 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚዎስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS / ኤስ ኤም ኤስ ኤስ / ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403፤
የሥራ ሰአት፡- ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0118-27-91-23
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለሥልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-30 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kenema Pharmacy Enterprise
- Buyer address: ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS (ኤስ ኤም ኤስ ኤስ) ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 08, 2026
- Posted at: 2026-04-08T12:52:38.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.