የሳሪስ ልማተገበያ አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር በሕንጻው ውስጥ ያለውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ (ፓርኪንግ) በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ከአሸናፊዎች ጋር ውል ለመግባት ይፈልጋል
Description
የመኪና ማቆምያ ቦታ (ፓርኪንግ) የጨረታ ማስታወቂያ
የሳሪስ ልማተገበያ አዲስ ሕይወት አክሲዮን ማህበር በሕንጻው ውስጥ ያለውን የመኪና ማቆሚያ ቦታ (ፓርኪንግ) በጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ከአሸናፊዎች ጋር ውል ለመግባት ይፈልጋል።
በመሆኑም በመስኩ የተሰማሩ የአገልግሎት አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. የዘመኑን ግብር የተገበረበትና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ወይም አዲስ የሚያወጣ
2. ተጫራቾች በዚህ ስራ መስክ የሁለት ዓመት ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
3. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ መመሪያ ሰነድን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዐት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 502 በመግዛት ከጨረታው መክፈቻ በፊት ወይንም በእለቱ በግንባር በመቅረብ ማስገባት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ለ 60 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ከሚያቀርቡት ፕሮፖዛል ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል
5. ተጫራቾች ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በመሙላት ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኦሪጅናል፣ ቴክኒካል ፕሮፖዛል ኮፒ፣ ፋይናንሻል ፐሮፖዛል ኦሪጅናል፣ ፋይናንሻል ፕሮፖዛል ኮፒ በማለት ለይተው እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለብቻ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የድርጅታቸሁን ህጋዊ ማህተም በማሳረፍ በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 25 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥ ሆኖ በቀን 24/08/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 4፤30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ወይንም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይሆናል፤
7. የጨረታው አሸናፊ ውጤት እንደተገለጸ ከ3 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ይፈጽማል።
8. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል ማሻሻል ወይንም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- በአ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወ/06 ሳሪስ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባቡር ፌርማታ ፊት ለፊት ከሬዮስ ኢንጂነሪንግ አጠገብ የሚገኘው የሳሪስ ልማተ ገበያ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502
ለተጨማሪ መረጃ : ስልክ ቁጥር 0114-42-21-21 ወይም 0910-87-00-41 ወይም 0948-21-22-21 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የሳሪስ ልማተ ገበያ አዲስ ህይወት አክሲዮን ማህበር !
Tender details
- Deadline: 2026-05-02
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-02 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Saris Development Market Addis Hiwot S.C.
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 08, 2026
- Posted at: 2026-04-08T13:25:28.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.