በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/አ/ደ/ማ/ባ/እቃ/ግ/ጨ/05/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው የእቃ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን |
ምርመራ |
|
1 |
የካፌ አገልግሎት እቃዎች |
20,000.00 |
|
|
2 |
የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች |
200,000.00 |
|
|
3 |
የምክር አገልግሎት |
30,000.00 |
|
|
4 |
የተለያዩ መጽሐፍቶች |
15,000.00 |
|
|
5 |
የመኪና ማስዋቢያ እቃዎች |
18,000.00 |
|
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋገጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን TIN ማቅረብ የሚችሉ
5. የአቅራቢነት ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 – 11፡00ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08/15 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ፋይናሻል ኦርጅናልና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ለየብቻው በማቅረብ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ግዥና ንብረት አ/ጠ/አ/ዳይሬክቶሬት 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09/22 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የሚቀርበው ዋጋ ማቅረቢያ ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ናሙና የተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል።
11. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- አ/አ አራዳ ክፍለ ከተማ (ፒያሳ) ልዩ ስሙ እሪ በከንቱ ተብሎ በሚጠራው የኢትዮጵያ ስታቲስቲካል አገልግሎት ቢሮ አካባቢ እስጢፋኖስ መካሻ አማረ (EMA )ህንፃ 9ኛ ፎቅ፤ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115 622 343 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-04-21
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-21 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Administration Code Enforcement Authority
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 09, 2026
- Posted at: 2026-04-09T09:29:24.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.