የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አቶ ጉሬ ጉዱ ቱሉ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ደሳለኝ ምናዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/102504 በ28/04/2018 ዓ.ም እና በመ/ቁ 105353 12/6/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሸገር ከተማ ሱሉልታ ከ/ከተማ ቀበሌ 01 ካርታ ቁጥር OR033016011015 የቤቱ ስፋት 215.23 ካ/ሜ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 2,200,000 ( ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ ቤት/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-05-14 14:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 09, 2026
  • Posted at: 2026-04-09T09:37:26.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders