የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ሒሩት ሔኖክ እና በፍ ባለዕዳ እነ ነብዩ ፍስሀ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.214876 በቀን 17/04/207ዓ.ም እና የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.260118 በቀን 26/06/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1ኛ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የቤት ቁጥር 182 የካርታ ቁጥር አ/14/66/2343/01 የሆነውን መኖሪያ ቤት የይዞታው ስፋት 96 ካ.ሜ. አዋሶኞቹ በሰሜን መንገድ በደቡብ የቤት ቁጥር 185 የግል ቤት በምዕራብ የቤት ቁጥር 170.173 የቀበሌ ቤት በምስራቅ የቤት ቁጥር 185 የግል ቤት የሚያዋስኑት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 6,512,262.13 ( ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ አስራ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ሁለት ከ13/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። 2ኛ በአራዳ ከ ከተማ ወረዳ 07 የካርታ ቁጥር AA000010700395 የቦታው ስፋት 447 ካ.ሜ የሆነ የቤት ቁጥር 184 የሆነ መኖሪያ ቤት በአቶ ፍስሃ ተገኝ ስም የተመዘገበ አዋሳኞቹ በሰሜን መንገድ በደቡብ ናይል ሰርቪስ በምስራቅ ቀበሌ በምዕራብ ናይል ሰርቪስ የሚያዋስኑት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ 35,570,748.05 (ሰላሳ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ሺህ ሰባት መቶ አርባ ስምንት ከ05/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመግኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አ ጽ/ቤት /ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አስርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-14
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-05-14 11:30
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 10, 2026
  • Posted at: 2026-04-11T07:24:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders