የቦታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 201 ካ.ሜ የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ኦሮሚያ ባንክ አማ እና የፍ/ባለዕዳ እነ ሽኩዳድ ጠቅላላ ንግድ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/300570 በሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/325860 በ03/04/2017ዓ/ም በህዳር 19 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ፍርድ ያረፈበት ቤት በለሚ ኩራ ከ/ከተማ ወረዳ 9 ውሰጥ የሚገኝ በካ/ቁ/ቦሌ/09/84/5/1/9900/248374/02 የተመዘገበ ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 129,480,951 (አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሚሊዮን አራት መቶ ሰማኒያ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃምሳ አንድ ብር) ሆኖ በካ/ቁ/ቦሌ/09/84/5/1/9900/248374/02 በሴሪያል ቁጥር 047511 በወ/ሮ ተዋቤ ሰውአገኝ ወርቄ ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት በካርታቸው መሰረት 201 ካ/ሜ የትራዛከሽን ታከለ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ በመሆኑም በፌ/ከ/ፍ/ቤ በኮ/መ/ቁ.325860 በቀን 15/07/2018ዓም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ድጋሚ ሐራጅ ሆኖ 1/4ኛ 32,370,237.75 (ሰላሳ ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰባ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ሰባት ከ75/100) ሆኖ የትራክሽን ታከለ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት በ1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ዝንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-05-12 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 11, 2026
- Posted at: 2026-04-11T08:37:44.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.