Office and commercial space rental
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጅግጅጋ ቅ/ፅ/ቤት እስከ 2 አመት የሚቆይ ቢሮ ኪራይ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ ኢስአ/ግጨ/jጅግ/001/2018
መ/ቤታችን በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት |
የጨረታ ሠነድ መግዥያ ዋጋ መግለጫ (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
እስከ 2 አመት የሚቆይ ቢሮ ኪራይ ጨረታ |
200.00 |
5,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ በመምጣት 200 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- ባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ወይም የቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN number/ እና በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተሰጠ የታክስ ክሪላንስ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠዉ የጨረታ ሰነድ ከፍል 6 ላይ ከተመለከተዉ የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል።
- ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ከዚሁ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ጅግጅጋ ስታቲስቲክስ ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ስልክ ቁጥር 0910144705/0910866265
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ጅግጅጋ ቅ/ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-05
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም 8:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-05 14:30
- Bid opening (note): መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም 8:30 ሰዓት
- Region: Somali
- Publishing entity: Ethiopian Statstics Service Jigjiga Bureau
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Apr 11, 2026)
- Posted at: 2026-04-11T08:47:12.000Z