የቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍባለመብት ፍሬወይኒ መሠረት እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ሙሴ ሸዋዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 93575 በ15/5/2017 ዓ.ም እና በመ/ቁ 106572 በ28/6/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ውስጥ በወ/ሮ ሸዋዬ ገብረየስ ስም የተመዘገበ የቤ/ቁ 037 እና የካርታ ቁጥር 35367 የሚታወቀው ቤት ባረፈበት ይዞታ ውስጥ ቀደም ሲል የውሻ ቤት የነበረና በኋላ ተከሳሽ አስፋፍተው ሠርተውታል በሚል ከውርስ ሀብቱ፣ ውጪ እንዲሆን ከተደረገው አንድ ክፍል ውጪ ያሉት ሌሎች ቤቶች እና ይዞታውን ካርታ ያለው የይዞታው ስፋት 340 ካ.ሜ ሆኖ የብሎኬት ቤት 141 ካ.ሜ የጭቃ ቤት 43.75 ካ.ሜ ላይ ያረፈ የመንገድ ጥናት ያለበት የሆነው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 16,761,070 (አስራ ስድስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ አንድ ሺ ሰባ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.106572 በ10/06/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት 1/4ኛ 4,190,267.50 (አራት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ሰባት ከ50/100) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚያመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም።

በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት /ስም CPO አሠርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሠርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሽጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዘዋወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

የፌዴራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-13
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid opening: 2026-05-13 11:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 10, 2026
  • Posted at: 2026-04-11T08:58:09.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders