በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለማሻ ወረዳ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት

  • ሎት 1ኛ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • ሎት 2ኛ ፈርኒቸር ዕቃዎች
  • ሎት 3ኛ የጥጉ ሠራተኞች ደንብ ልብስ
  • ሎት 4ኛ የቪዲዮ ካሜራዎች ከነ አክሰስሪው

ተጫራቾችም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፍ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል። በዚሁ መስረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን ማሟላት የሚችሉትን ተጫራቾችን ይጋብዛል።

1/ በመስኩ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለውና የ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።

2/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ብር 5000 (አምስት ሺህ) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው።

3/ ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ከማሻ ወረዳ ገ/ባ/ሥ/ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ከማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) መውሰድ ይችላሉ።

4/ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

5/ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት (አራት) ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በ16ኛው ቀን ጨረታው ይከፈታል።

6/ የጨረታው አሸናፊ የሆኑት አቅራቢ ዕቃዎችን አጓጉዞ በሸካ ዞን ከማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።

7/ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት።

8/ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0475580293 ወይም 0912789043 ወይም 0925270431 ደውስው መጠየቅ ይችላሱ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-27 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Sheka Zone Masha Woreda FEDB
  • Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ
  • Published: Apr 12, 2026
  • Posted at: 2026-04-13T09:53:59.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders