አንደኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ፡ በሸገር ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙት ኮዬ ፈጬ፣ ቡራዩ፣ እና መልካ ኖኖ ከፍለ ከተሞች ውስጥ ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል። ማሳሰቢያ፡- ሲፒኦ (CPO) ተዘጋጅቶ መቅረብ ያለበት በ "Sheger City Finance Office Municipality" ስም መሆን አለበት።
Description
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት
የ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት ለተለያዩ አገልግሎቶች የተዘጋጁና በቆዬ ፈጬ፣ በቡራዩ፣ እና በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ለማስተላለፍ ይፈልጋል።
የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ቴሌብር (telebirr) በመጠቀም shaggarland.2merkato.com ወይም shaggarland.afrotender.com ድረ-ገጾች ላይ በመግባት በኦንላይን መግዛትና ሰነዱን ፕሪንት በማድረግ መወዳደር ይኖርባቸዋል።
የጨረታ ሰነድ ግዢውን ከሚያዝያ 05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት መፈፀም ይችላሉ፤ ተጫራቾች የጨረታ መልስ ማቅረቢያሰነድ፣ ሲፒኦ (CPO)፣ የግንባታ አቅም ማሳያ ማስረጃ፣ ሰነዱን ለመግዛት የከፈሉበትን የቴሌብር ደረሰኝ ወይም ስሊፕ እና ሌሎች መያያዝ ያለባቸዉና በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተገለጹትን በፖስታ (በኤንቨሎፕ) በማሸግ እስከ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ንፋስ ስልክ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወይም ጎተራ ማሞ ኮንዶሚኒየም አካባቢ የሸገር ከተማ መሬት ጽ/ቤት በሚገኝበት የሸገር ከተማ የአንድ ማዕከል አገልግሎት (MESOB) ህንፃ ምድር ቤት (በጉግል ቦታ ማሳያ) https://maps.app.goo.gl/toCJZwKSxr2Sxckv7 ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 3 የስራ ቀናት መስሪያ ቤቱ ለዚሁ ጨረታ ባዘጋጀው ቦታ ላይ የሚከፈት ሆኖ፣ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃው በማስታወቂያ ይገለፃል።
- የጨረታውን ዝርዝር መረጃ ሚያዝያ 08/2018 ዓ.ም በወጣው ከለቻ ኦሮሚያ እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም ከላይ በተጠቀሱት ድረ ገጾች መረጃውን ማግኘት ይችላሉ።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በመሬት ጽ/ቤቱ ስልክ ቁጥር +251-11-47-095-44 ወይም +251-11-47-080-06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
ማሳሰቢያ፡ ሲፒኦ (CPO) ተዘጋጅቶ መቅረብ ያለበት በ "Sheger City Finance Office Municipality" ስም መሆን አለበት
በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤
1. ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ) ብር በቴሌብር (Telebirr) በመክፈል shaggarland.2merkato.com ወይም shaggarland.afrotender.com በተባሉት ድረ-ገጾች በመጠቀም የጨረታ ሰነዱን ከሚያዝያ 05 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ድረስ በመግዛት ማውረድ (Download ማድረግ) ትችላላችሁ።
2. ማንኛውም በዚህ የሊዝ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በቁጥር አንድ ላይ በተጠቀሰው ድረ-ገጽ ሰነዱን ለመግዛት በመጀመሪያ በራሱ ስም ብቻ ከራሱ ሂሳብ ላይ ቀንሶ መግዛት አለበት።
3. ተጫራቾች መሬቱ ወደሚገኝበት ቦታ በመሄድ የቦታውን ሁኔታ ካየ በኋላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4, አንድ ተጫራች በአንድ የጨረታ ዙር ከአንድ ቦታ በላይ መወዳደር አይችልም። ከአንድ ቦታ በላይ ተወዳድሮ ከተገኘ ከጨረታው ውጭ ይሆናል።
5. ተጫራቾች ሞልተው የሚያቀርቡት የጨረታ መልስ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ (Bidders Manual) ላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያሟላ መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የቦታውን ስፋት በመነሻ ዋጋ በማባዛት ከሚመጣው ጠቅላላ ዋጋ 5% ያነሰ መሆን የለበትም። ይህ የክፍያ መጠን በጋዜጣ ላይ ለእያንዳንዱ የቦታ ኮድ (Plot Code) ከተጠቀሰው ጋር መጣጣም አለበት። ይህ ካልሆነ ወይም ክፍያው ከ5% በታች ከሆነ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል። በተጨማሪም አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመርኩዞ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ከሸገር ከተማ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጭ ያሉ ባንኮች የሚዘጋጅ CPO ከአዲስ አበባ ወይም ከሸገር ከተማ ባንኮች ጋር በኔትወርክ የተገናኘ መሆን አለበት። የኔትወርክ መቋረጥ ቢከሰት መስሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
7. ተጫራቾች ከጨረታ መልስ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚገባቸው ማስረጃዎች፦
- 7.1 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO)
- 7.2 የጨረታ መልስ ሰነድ (በታሸገ ኤንቨሎፕ)
- 7.3 የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያ ኮፒ / ፋይዳ (FAYIDA)
- 7.4 በራሱ ስም ዶክመንት ሲገዛ የከፈለበትን የቴሌብር ደረሰኝ (Slip) - ማለትም ክፍያ ሲፈጸም ቴሌብር ከሚልከው ቴክስት ላይ ያለውን ሊንክ በመጠቀም የኢትዮ ቴሌኮም ማህተም ያለበት ደረሰኝ ፕሪንት በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- 7.5 የግንባታ አቅምን የሚያሳይ ኦሪጅናል የባንክ ስቴትመንት (Bank Statement)
- 7.6 በህጋዊ ውክልና ከሆነ፣ የታደሰ መታወቂያ እና ኦሪጅናል የውክልና ማስረጃ
- 7.7 ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጎች ከሚኖሩበት ሀገር ኤምባሲ ወይም ቆንስላ የተሰጠ እና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- 7.8 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ (Erasures/Alterations) መኖር የለበትም፤ ስርዝ ካለው ተቀባይነት የለውም።
- 7.9 ተጫራቹ በሰነዱ ላይ የሚሞላው ዋጋ በግልጽ የሚነበብ መሆን አለበት፤ እንዲሁም በፊርማ እና በፕላስተር (Scotch tape) የታሸገ መሆን አለበት።
- 7.10 ለጨረታው CPO ሲያዘጋጁ የቦታውን ኮድ (Plot Code) በትክክል መጥቀስ አስፈላጊ
ነው። - 7.11 በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች በፖስታ በማሸግ በሸገር ከተማ አስተዳደር አንደኛ አገልግሎት ማዕከል (ግራዉንድ /ደንበኞች መቀበያ ቦታ) እስከ ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም ከሰዓት 11፡00 ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በሸገር ከተማ አስተዳደር የመሬት ጽ/ቤት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው አዳራሽ ውስጥ ይሆናል።
9. የጨረታው አሸናፊ በሚከተሉት መስፈርቶች መሰረት ተለይቶ ይታወቃል፦
- ሀ. ተጫራቹ ለቦታው ያቀረበው ከፍተኛ ዋጋ ከ 80%፤
- ለ. ለቅድመ ክፍያ (Down payment) ያቀረበው ከፍተኛ መጠን ከ 20% የሚታሰብ ይሆናል።
10. በጨረታው ላልተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO፣ የአሸናፊዎች ዝርዝር በ'ከለቻ ኦሮሚያ' ጋዜጣ ላይ ከወጣ ከ15 የስራ ቀናት በኋላ፣ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ መስሪያ ቤቱ ለባንክ በመላክ CPO ወደ ተሰራበት የባንክ ሂሳብ እንዲመለስ ይደረጋል። ተጫራቾች ገንዘባቸውን ለመቀበል የCPO ኮፒ እና መታወቂያ በመያዝ በሸገር ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት መቅረብ አለባቸው። ከተጠቀሰው ጊዜ ገደብ በላይ ዘግይተው ቢመጡ ለሚፈጠረው ችግር መስሪያ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
11 የሊዝ ክፍያ ሁኔታ፦
- ሀ. የጨረታው አሸናፊ የሚከፍለው የቅድመ ክፍያ (Down payment) መጠን ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 30% (ሰላሳ በመቶ) እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
- ለ. ከቅድመ ክፍያ የቀረው ሂሳብ በ 10 (አስር) ዓመታት ውስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ አለበት።
12. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ የቅድመ ክፍያውን ከፍሎ፣ የሊዝ ውል በመፈረም የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የመውሰድ መብት አለው።
13. የሊዝ ውል የፈጸመ ሰው ግንባታ የሚጀምርበትና የሚያጠናቅቅበት ጊዜ በአዋጁ አንቀጽ 39 እስከ 41 በተደነገገው መሰረት ይሆናል።
14, አሸናፊው ውጤቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈጸመ፣ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዲደርሰው ወይም ጥሪው በመስሪያ ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲለጠፍ ይደረጋል፡፡
15, አሸናፊው ማስጠንቀቂያው ከደረሰው ወይም በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ 3 (ሶስት) የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ክፍያ ፈጽሞ ውል ካልፈረመ፣ አሸናፊነቱ ይሰረዛል። ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብም ለከተማው ገቢ ይሆናል፡፡
16, ከቁጥር (9) እስከ (15) የተጠቀሱት እንደተጠበቁ ሆነው፣ ለጨረታ የቀረበው መሬት ለግል መኖሪያ ቤት አገልግሎት ውጭ ከሆነ፣ አሸናፊው በስልጣን ባለው አካል የጸደቀ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ (Environmental Impact Assessment) ማቅረብ ይኖርበታል።
17. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡ ሲፒኦ (CPO) ተዘጋጅቶ መቅረብ ያለበት በ "Sheger City Finance Office Municipality" ስም መሆን አለበት
የስልክ ቁጥር፦ +251-11-47-095-44፣ +251-11-47-080-06
Bulchiinsa Magaalaa Shaggariitti Waajjiira Lafaa Magaalaa Shaggar
Beeksisa Caalbaasii Liizii Lafa Marsaa 1ffaa
Waajjiirri Lafaa Magaalaa Shaggar, iddoowwan tajaajila adda addaatif qophaa'an kanneen Kutaa Magaalaa Koyyee Faccee, Buraayyuu, Malkaa Noonnoo fi Furiitti argaman caalbaasiidhaan dorgomsiisee liiziin dabarsuu barbaada.
Sanada caalbaasii bitachuuf telebirr, toora intarneetii shaggarland.2merkato.com ykn shaggarland.afrotender.com seenuun onlaayiniin bitachuu fi sanadicha piirinti gochuun dorgomuu qabu.
Bittaa sanada caalbaasii Ebla 05/2018 irraa eegalee hanga Ebla 22/2018tti sa'aatii 10:00tti guyyoota hojii walitti aananitti raawwachuu dandeessu; dorgomtootni sanada deebii caalbaasii, CPO, ragaa dandeettii ijaarsaa agarsiisu, nagahee ykn isliipii kaffaltii sanada ittiin bitatan fi ragaalee biroo dabalataan qajeelfama dorgomtootaa irratti ibsaman poostaadhaan saamsuun hanga Ebla 22/2018 sa'aatii 11:30tti (waaree booda) naannoo Gootaraa/Kondominiyeemii Maammoo/Kolleejjii Poolii Tekinikaa Nifaas Silk fuuldura/ argama iddichaa (Google Location) https://maps.app.goo.gl/toCJZwKSxr2Sxckv7 iddoo Waajjiirri Lafaa Magaalaa Shaggar itti argamutti Gamoo Wiirtuu Tajaajila Tokkoffaa (MESOB) Magaalaa Shaaggar darbii jalatti saanduqa caalbaasii kanaaf qophaa'e keessa galchuu qabu.
Caalbaasiin kun dorgomtootni ykn bakka bu'ootni seeraa isaanii bakka argamanitti Ebla 28/2018 ganama sa'aatii 3:00 irraa eegalee guyyoota hojii 3 walitti aananiif Galma Waajjirichi Dhimma Kanaaf Qopheessutti kan banamu ta'ee, ibsi dabalataa isaa beeksisa keessaa irratti ni ibsama.
- Odeeffannoo bal'aa caalbaasichaa Gaazexaa Kallacha Oromiyaa fi Gaazexaa 'Addis Zemen' Ebla 08/2018 bahe irratti ilaaluun ni danda'ama. Dabalataanis, weebsaayitoota armaan olitti ibsaman irratti odeeffannoo kana argachuu ni dandeessu.
- Waajjiirrii kun filannoo fooyya'aa yoo argate caalbaasicha gar-tokkeenis ta'e guutummaatti haquuf mirgi isaa eegamaadha.
- Odeeffannoo dabalataatiif lakk. bilbila Waajjiira Lafaa +251-11-47-095-44 ykn +251-11-47-080-06 irraa argachuun ni danda'ama.
Hubachiisa: Maqaa CPO n ittiin hojjetamee dhiyaachuu qabu; "Sheger City Finance Office Municipality" ta'uu qaba.
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-05-06 09:00
- Region: Oromia
- Publishing entity: Shaggar City Land Office
- Bid bond: 5%
- Bid document price: ለአንድ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 2,300.00 (ሁለት ሺህ ሶስት መቶ) ብር
- Published: Apr 13, 2026
- Posted at: 2026-04-13T12:30:31.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.