Land lease and real estate
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል
Description
የ2018 ዓ.ም 4ኛ ዙር የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት በከሚሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ቦታወች ስፋታቸው 2557 ካሬ ሜትር የሆኑ ለድርጅት እና ለመኖሪያ 441 ካሬ ሜትር ድምር 2998 ካሬ ሜትር የሆኑ ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ አወዳድሮ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
የጨረታውን ሰነድ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ሸያጭ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
1. ተጫራቾች ቦታዎቹ የሚገኙበት ድረስ በመሄድ አጠቃላይ የቦታዎቹን ሁኔታ በማየት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ። ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው ስፔስፊኬሽን /Specification/ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ቦታ ስፋት በሊዝ መነሻ ዋጋ ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 20 በመቶ ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ይህ ሳይሆን ቢቀር ወይንም ከ 20 ከመቶ ቢያንስ ተጫራቹ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከውድድር ይሰረዛል። እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
2. ተጫራቾች የቅድመ ክፍያ ከጠቅላላው ብር ላይ 30% መክፈል የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ሀ) ተጫራቾች ለቦታው ያቀረቡት ዋጋ 80%
3. የጨረታ አሸናፊወችን ለመለየት የሚከተሉትን የማወዳደሪያ መስፈርቶችን መሰረት በማድረግ ይሆናል፡-
ለ) የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን 20% የሚያዝ ይሆናል
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ፣ ሲፒኦ እና ሌሎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በአብከመ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ05/08/2018 ዓ.ም እስከ 16/08/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16/08/2018 ዓ.ም 11:00 ሰዓት ይሆናል።
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በ 17/08/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በከሚሴ ከተማ አስ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7. በጋራ ተደራጅተው /በአክሲዮን/ እነ በሚል ሰነድ ለመግዛት የሚፈልጉ አካላት ከሚመለከተው አካል እነ የተባላችሁበትን ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ መረጃ በስም ዝርዝር ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
8. ቦታውን ለመጎበኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ለሽያጭ የተዘጋጁ ቦታዎች በሚገኙበት የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በሚመድባቸው አስጎብኝዎች ቦታዎቹን መመልከት ይችላሉ።
9.የአካበቢውን ወቅታዊ የሊዝ ጨረታ መነሻ ዋጋ እና ሌሎች የከተማ መሬትን በሊዝ ለማስተዳደር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሰረት በማድረግ በከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከት ይችላሉ።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥሮች 09 13 50 18 99/ 033 554 0255/ ወይንም
Gmail address [email protected] መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን
የከሚሴ ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-04-25 10:00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kemise City Administration Urban and Infrastructure Development Office
- Bid bond: 20%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Apr 13, 2026)
- Posted at: 2026-04-14T12:20:20.000Z