በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሰራተኛ ካፌ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሰራተኛ ካፌ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1. በዘርፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና ጨረታ ለመወደደር የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

2. የVAT/ ተመዝጋቢ ወይም የR ኮድ የእጅ በእጅ የሽያጭ ደረሰኝ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለበት።

3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30 እስከ 11፡00 በቃሌ ቅድመኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት አንድ መቶ (100) ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

5. ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን በመሙላት ኦርጅና ፋይናንሻል ፣ቴክኒካል ሰነድ እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማግልፅ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፤ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብ አለባቸው ሰነዶቹ በማህተም መረጋገጥ አለባቸው።

9. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑ ማወቅ ይኖርባቸዋል።

10. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-ቃሴ ቅድመ 1ኛ፡1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አስኮ እያሱ ፀበል በአክሱም አዳራሽ 400 ሜትር ገባ ብሎ

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 2 73 17 69

በጉ/ክ/ከ/ወ/ 05 ቃሌ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-24 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kale Kindergarten & Elementary School
  • Buyer address: አስኮ እያሱ ፀበል በአክሱም አዳራሽ 200 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Apr 13, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T12:42:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders