የይዞታው ስፋቱ 620 ካ/ሜ የድርጅት ቦታና ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
የሐራጅ ሸያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት አቶ ሞገስ አምደብርሀን እና የፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ጥሩወርቅ አምደብርሃን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 137665 በ4/03/2016 ዓ.ም በ24/08/2016 ዓ.ም በመ/ቁጥር 130585 በ8/7/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቤት ቁጥር 573 በካ/ቁ/3242 በወ/ሮ ከበቡሽ ቀደሚ የተመዘገበ የይዞታው ስፋቱ 620 ካ/ሜ የድርጅት ቦታና ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 62,532,320 (ስልሳ ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ሃያ ብር) የመንገድ ጥናት 163.32 የሚነካው ካፒታል ጌን ታክስ ከሽያጩ የሚቆረጥ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤት የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-18
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-05-18 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 14, 2026
- Posted at: 2026-04-14T14:03:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.